በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አሌክሳንደር ካባኖቭ

ነሐሴ 8, 2022 | የታደሰው፦ ታኅሣሥ 29, 2022
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ብይኑ ተሻረ | አሌክሳንደር ካባኖቭ አእምሮውን ማዘጋጀቱ እንዳይረበሽ ረድቶታል

ወቅታዊ መረጃ—ብይኑ ተሻረ | አሌክሳንደር ካባኖቭ አእምሮውን ማዘጋጀቱ እንዳይረበሽ ረድቶታል

ታኅሣሥ 27, 2022 የክራስናያርስክ ክልል ፍርድ ቤት በወንድም አሌክሳንደር ካባኖቭ ላይ የተላለፈውን የሁለት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት በመሻር ክሱ ዳግመኛ እንዲታይ ጠይቋል። ነሐሴ 5, 2022 የዜሌኖጎርስክ ከተማ ፍርድ ቤት በወንድም ካባኖቭ ላይ ብይን ማስተላለፉ ይታወሳል፤ ሆኖም የይግባኝ ጥያቄ ቀርቦ ነበር። ወንድም ካባኖቭ ክሱ ዳግመኛ እስኪታይ ካለበት አካባቢ መውጣት አይፈቀድለትም።

በክራስናያርስክ ክልል የሚገኘው የዜሌኖጎርስክ ከተማ ፍርድ ቤት በቅርቡ የወንድም አሌክሳንደር ካባኖቭን ጉዳይ በተመለከተ ብይን ያስተላልፋል። አቃቤ ሕጉ ወንድም አሌክሳንደር የሁለት ዓመት ከስድስት ወር እስራት እንዲፈረድበት ጥያቄ አቅርቧል።

የክሱ ሂደት

  1. ታኅሣሥ 26, 2019

    ተይዞ ታሰረ፤ ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብንና ለሌሎች ስለ ይሖዋ መናገርን ጨምሮ እገዳ የተጣለበት ጽንፈኛ ድርጅት በሚያካሂዳቸው እንቅስቃሴዎች ተካፍለሃል በሚል ክስ ተመሠረተበት። በመሆኑም ማረፊያ ቤት እንዲገባ ተደረገ

  2. ታኅሣሥ 27, 2019

    ዳኛው፣ መርማሪዎቹ ማረፊያ ቤት እንዲቆይ ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ በማድረጉ ከማረፊያ ቤት እንዲወጣ ተደረገ

  3. ታኅሣሥ 6, 2021

    አሌክሳንደር ለፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ቃሉን ሰጠ። ዳኛው ፍርድ ከማስተላለፍ ይልቅ ጉዳዩ ወደ መርማሪዎቹ እንዲመለስ አደረገ፤ ይህም የክሱ ሂደት እንዲራዘም አድርጓል

  4. መጋቢት 25, 2022

    የክሱ ሂደት እንደገና ቀጠለ

አጭር መግለጫ

በሩሲያ የሚገኙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ግሩም የእምነት ምሳሌ ናቸው። በኢሳይያስ 12:2 ላይ የሚገኘውን “እነሆ፣ አምላክ አዳኜ ነው! በእሱ እታመናለሁ፤ ምንም የሚያስፈራኝ ነገር የለም፤ ያህ ይሖዋ ብርታቴና ኃይሌ ነው” የሚለውን ሐሳብ ምን ያህል እንድሚያምኑበት በተግባር አሳይተዋል።