በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ሰርጌ ቼቹሊን እና ባለቤቱ ዬሌና

መጋቢት 19, 2024 | የታደሰው፦ ኅዳር 5, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ብይኑ ተሻረ | ‘የሚያጽናናኝ ይሖዋ ራሱ ነው’

ወቅታዊ መረጃ—ብይኑ ተሻረ | ‘የሚያጽናናኝ ይሖዋ ራሱ ነው’

ጥቅምት 30, 2024 በቭላዲቮስቶክ የሚገኘው ዘጠነኛው ጠቅላይ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ሰርጌ ቼቹሊን እና በባለቤቱ በእህት ዬሌና ቼቹሊና ላይ ተላልፎ የነበረውን ፍርድ ሽሮታል። ክሳቸው በድጋሚ እንዲታይ ወደ መጀመሪያው ፍርድ ቤት ይመለሳል።

ሚያዝያ 22, 2024 በካምቻትካ ግዛት የሚገኘው የፔትሮፓቭሎቭስክ ካምቻትስኪ ከተማ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ሰርጌ ቼቹሊን እና በባለቤቱ በእህት ዬሌና ቼቹሊና ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ሁለቱም የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተበይኖባቸዋል። በአሁኑ ወቅት እስር ቤት አይገቡም።

አጭር መግለጫ

እንደ ሰርጌና ዬሌና ሁሉ እኛም ፍጹም የሆነውን የአምላክ ቃል ከፍ አድርገን እንመለከተዋለን፤ በፈተና ወቅት በታማኝነት መጽናት እንድንችል ኃይላችንን ያድስልናል እንዲሁም ጥበብ ይሰጠናል።​—መዝሙር 19:7

የክሱ ሂደት

  1. መስከረም 25, 2022

    የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው

  2. ጥቅምት 17, 2022

    ቤታቸው ተፈተሸ

  3. መስከረም 6, 2023

    ሰርጌ የጉዞ ገደቦች ተጣሉበት

  4. መስከረም 7, 2023

    ዬሌና የጉዞ ገደቦች ተጣሉባት

  5. ታኅሣሥ 26, 2023

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ