ሐምሌ 14, 2021| የታደሰው፦ ታኅሣሥ 2, 2022
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ብይን ተላለፈ | ሦስት ወንድሞች ለስደት መዘጋጀታቸው ታማኝነታቸውን እንዲጠብቁ ረድቷቸዋል
ኅዳር 30, 2022 በፕሪሞርይስ ክልል የሚገኘው የኡሱሪስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት በወንድም አንቶን ቼርምኒክ፣ በወንድም ሰርጌ ኮሮልቹክ እና በወንድም ዲሚትሪ ቲሽቼንኮ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ሦስቱም የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ተላልፎባቸዋል። በእርግጥ አሁን ወህኒ አይወርዱም።
የክሱ ሂደት
መስከረም 23, 2020
የአንቶን፣ የሰርጌና የዲሚትሪ ጉዳይ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
ሐምሌ 7, 2020
አንቶን፣ ሰርጌ እና ዲሚትሪ “ጽንፈኛ” በሆነ እና እገዳ በተጣለበት ሃይማኖታዊ ድርጅት ውስጥ የአመራር ቦታ አላቸው የሚል ክስ ተመሠረተባቸው
ሰኔ 18, 2019
ሰርጌ ለሁለት ቀን ያህል በማረፊያ ቤት እንዲቆይ ተደረገ
አጭር መግለጫ
በአንቶን፣ በሰርጌና በዲሚትሪ ላይ የሚደርሰው ፈተናና ስደት ቢቀጥልም ይሖዋ ለታማኝነታቸው እንደሚባርካቸው እርግጠኞች ነን።—ምሳሌ 28:20