ነሐሴ 20, 2021 | የታደሰው፦ ኅዳር 28, 2022
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ብይን ተላለፈ | በዳግስታን የሚኖሩ ሦስት ወንድሞችና አንዲት እህት በማረፊያ ቤት ሳሉ ይሖዋ ደግፏቸዋል
ኅዳር 24, 2022 በዳግስታን ሪፑብሊክ፣ በማሃችካላ የሚገኘው የኪሮቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት በወንድም ማራት አብዱልጋሊሞቭ፣ በወንድም አርሴን አብዱላዬቭ፣ በወንድም አንቶን ዴርጋሌቭ እና በእህት ማሪያ ካርፖቫ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ከስድስት ዓመት እስከ ስድስት ዓመት ተኩል የሚደርስ የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል። በእርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርዱም።
የክሱ ሂደት
ግንቦት 27, 2020
ማራት፣ አርሴን፣ አንቶን እና ማሪያ ለ362 ቀናት በማረፊያ ቤት ከቆዩ በኋላ ወደ ቁም እስር ተዛወሩ
ሰኔ 4, 2019
በማሃችካላ የሚገኘው የሶቬትስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት አራቱም ማረፊያ ቤት እንዲቆዩ አዘዘ
ሰኔ 1, 2019
የሩሲያ የደህንነት አባላት (የሩሲያ የሚስጥር ፖሊስ) በዳግስታን የሚኖሩ 13 የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች ፈተሹ
ግንቦት 27, 2019
በዳግስታን የሚገኘው የሩሲያ የደህንነት ቢሮ በማራት፣ በአርሴን፣ በአንቶን እና በማሪያ ላይ የወንጀል ክስ መሠረተ
አጭር መግለጫ
ይሖዋ አምላክ ምንጊዜም ልክ እንደ ስሙ ሕዝቦቹን ለመጠበቅና ለመደገፍ መሆን የሚያስፈልገውን ሁሉ እንደሚሆን ሙሉ በሙሉ እንተማመናለን።—ዘፀአት 3:14
ፍርድ ቤቱ ብይን የሚያስተላልፍበትን ቀን አስቀድሞ የማያሳውቅበት ጊዜ አለ።