በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም ሩስታም ዲያሮቭ፣ ወንድም ዬቭጌኒ ኢቫኖቭ እና ባለቤቱ ኦልጋ እንዲሁም ወንድም ሰርጌ ክሊኩኖቭ

ጥቅምት 21, 2021 | የታደሰው፦ ታኅሣሥ 26, 2022
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ተጨማሪ ቅጣት ተጣለባቸው | ሩሲያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በማረፊያ ቤትና በቁም እስር ቢቆዩም ደስታቸውን ጠብቀዋል

ወቅታዊ መረጃ—ተጨማሪ ቅጣት ተጣለባቸው | ሩሲያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በማረፊያ ቤትና በቁም እስር ቢቆዩም ደስታቸውን ጠብቀዋል

ታኅሣሥ 22, 2022 አራተኛው ጠቅላይ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በወንድም ሩስታም ዲያሮቭ፣ በወንድም ሰርጌ ክሊኩኖቭ፣ በወንድም ዬቭጌኒ ኢቫኖቭና ባለቤቱ ኦልጋ ላይ ተጨማሪ ቅጣት አስተላልፏል። የእስር ጊዜያቸውን ሲጨርሱ ከአስትራካን ከተማ የመውጣት እግድ እንዲጣልባቸው ዳኛው በይነዋል። ወንድሞችና እህት ማረፊያ ቤት ሆነው ችሎቱን በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተከታትለዋል።

መጋቢት 3, 2022 የአስትራካን አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ሩስታም ዲያሮቭ፣ ወንድም ሰርጌ ክሊኩኖቭ፣ ወንድም ዬቭጌኒ ኢቫኖቭ እና ባለቤቱ ኦልጋ ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ አድርጓል። አራቱም እንደታሰሩ ይቆያሉ።

የክሱ ሂደት

  1. ጥቅምት 25, 2021

    በአስትራካን የሚገኘው የትሩሶቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት በሩስታም ፣ በዬቭጌኒ እና በሰርጌ ላይ የስምንት ዓመት እስራት በይኗል። የዬቭጌኒ ሚስት ኦልጋ የሦስት ዓመት ከስድስት ወር እስራት ተበይኖባታል። ሦስቱ ወንድሞች ቀድሞውንም ማረፊያ ቤት ነበሩ። ኦልጋ ደግሞ ወዲያውኑ ወደ እስር ቤት ተወስዳለች

  2. ሰኔ 11, 2020

    ሩስታም፣ ዬቭጌኒ እና ሰርጌ ማረፊያ ቤት ገቡ። ኦልጋ ደግሞ በቁም እስር እንድትቆይ ተደረገ

  3. ሰኔ 9, 2020

    ከ100 የሚበልጡ ፖሊሶች በአስትራካን ከተማ የሚኖሩ 27 የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች በረበሩ። ሩስታም፣ ዬቭጌኒ፣ ኦልጋ እና ሰርጌ በጊዜያዊ ማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ተደረገ

  4. ሰኔ 8, 2020

    በሩስታም፣ በዬቭጌኒ፣ በኦልጋ እና በሰርጌ ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተ። ወንድሞች የጽንፈኝነት እንቅስቃሴዎችን በማደራጀትና በገንዘብ በመደገፍ ወንጀል ተከሰሱ። ኦልጋ ደግሞ በጽንፈኝነት እንቅስቃሴ በመካፈል ወንጀል ተከሰሰች

አጭር መግለጫ

ይሖዋ በመከራ ጊዜ ለታማኝ አገልጋዮቹ ቅርብ እንደሆነ ማወቃችን በእጅጉ ያጽናናናል።—መዝሙር 139:5, 10