ታኅሣሥ 16, 2021
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ | አምስት ወንድሞችና አንዲት እህት መጽሐፍ ቅዱስን ማንበባቸው ስደትን ለመቋቋም ረድቷቸዋል
ነሐሴ 25, 2022 በሳራንስክ የሚገኘው የሌኒንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ዴኒስ አንቶኖቭ፣ ወንድም ቭላዲሚር አትርያኪን፣ ወንድም አሌክሳንደር ኮሮሌቭ፣ ወንድም ጌኦርጊ ኒኩሊን፣ እህት ዬሌና ኒኩሊና እና ወንድም አሌክሳንደር ሼቭቹክ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ዴኒስ፣ አሌክሳንደር ኮሮሌቭ እና አሌክሳንደር ሼቭቹክ እያንዳንዳቸው የሁለት ዓመት እስራት ተበይኖባቸዋል። ጌኦርጊ እና ዬሌና የአራት ዓመት ከሁለት ወር እስራት፣ ቭላዲሚር ደግሞ የስድስት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል። ሁሉም ወዲያውኑ ወደ ወህኒ ተወስደዋል።
የክሱ ሂደት
ሰኔ 11, 2021
በሳራንስክ በሚገኘው የሌኒንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት የመጀመሪያው ችሎት ተሰየመ
ሚያዝያ 2, 2021
ዬሌና ጽንፈኛ በሆነ ድርጅት እንቅስቃሴ በመካፈልና አባላትን በመመልመል ወንጀል ተከሰሰች
መጋቢት 31, 2021
ቭላዲሚር የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴ በማስተባበር ወንጀል ተከሰሰ
ሐምሌ 2, 2019
አሌክሳንደር ሼቭቹክ እና ጌኦርጊ ከማረፊያ ቤት የተለቀቁ ሲሆን አካባቢውን ለቀው እንዳይሄዱ ታዘዙ
መጋቢት 28, 2019
ቭላዲሚር ከማረፊያ ቤት የተለቀቀ ሲሆን አካባቢውን ለቆ እንዳይሄድ ታዘዘ
የካቲት 8, 2019
አሌክሳንደር ሼቭቹክ፣ ቭላዲሚር እና ጌኦርጊ ወደ ማረፊያ ቤት ገቡ
የካቲት 4, 2019
የፌደራል ደህንነት ቢሮ ጽንፈኛ የሆነን ድርጅት እንቅስቃሴ አስተባብረዋል በሚል በአምስት ወንድሞችና በእህት ዬሌና ላይ ክስ መሠረተ
አጭር መግለጫ
ይሖዋ በሩሲያ ስደት እየደረሰባቸው ላሉት በእሱ የሚታመኑ ውድ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ታማኝ ፍቅር ማሳየቱን እንደሚቀጥል እርግጠኞች ነን።—ዘፍጥረት 32:10