ጥር 28, 2022
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ | አና ሳፍሮኖቫ የስድስት ዓመት እስራት ተፈረደባት
በ2017 እገዳ ከተጣለ ጊዜ አንስቶ በእህቶች ላይ ከተላለፉት ፍርዶች ከባዱ ነው
ሚያዝያ 14, 2022 የአስትራካን ክልላዊ ፍርድ ቤት እህት አና ሳፍሮኖቫ ያቀረበችውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። እህት አና አሁንም እንደታሰረች ናት።
ጥር 25, 2022 በአስትራካን ክልል የሚገኘው የትሩሶቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት የ56 ዓመቷ አና ጥፋተኛ ነች በማለት የስድስት ዓመት እስራት ፈረደባት። ወዲያውኑ ወደ እስር ቤት ተወሰደች።
የክሱ ሂደት
ግንቦት 28, 2021
የወንጀል ክስ ተመሠረተባት
ሰኔ 2, 2021
የ81 ዓመት አረጋዊት ከሆኑት እናቷ ጋር የምትኖርበትን ቤት ፖሊሶች ፈተሹ። አና ማረፊያ ቤት ገባች
ሰኔ 3, 2021
ከማረፊያ ቤት ተለቃ በቁም እስር እንድትቆይ ተደረገች። በቀን ለአንድ ሰዓት ማለትም ከጠዋቱ 3:00 እስከ 4:00 በእግሯ ከመንሸራሸር በቀር ከቤቷ መውጣት አይፈቀድላትም ነበር
ሰኔ 10, 2021
በጽንፈኞች ዝርዝር ውስጥ ተካተተች፤ የባንክ ሒሳቦቿ በሙሉ ታገዱ
ጥር 24, 2022
በፍርድ ቤቱ ፊት የመደምደሚያ ሐሳብ በሰጠችበት ወቅት እንዲህ ብላለች፦ “ኢየሱስ በማቴዎስ 5:44 ላይ ‘ጠላቶቻችሁን ውደዱ እንዲሁም ስደት ለሚያደርሱባችሁ ጸልዩ’ በማለት ተከታዮቹን አስተምሯቸዋል። ለምን? ምክንያቱም ቀደም ሲል አሳዳጅ የነበሩ ብዙ ሰዎች በኋላ ላይ የይሖዋ አገልጋዮች ሆነዋል።
“ከደህንነት ቢሮ ባለሥልጣናት፣ ከመርማሪዎች፣ ከጠባቂዎች፣ ከጠበቃዎች እንዲሁም እኔን ከሚሰሙኝና ምግባሬን ከሚያዩት ሌሎች ሰዎች መካከል ቢያንስ አንዱ ለይሖዋ ምሥክሮች ያለውን አመለካከት እንደሚቀይር ተስፋ አደርጋለሁ። . . . ምናልባትም ቢያንስ አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ፣ ለጥያቄዎቹ መልስ ለማግኘት፣ አምላክን ለማወቅ አልፎ ተርፎም የእሱ አገልጋይ ለመሆን ይነሳሳ ይሆናል።”
ጥር 25, 2022
ጥፋተኛ ነች ተብላ የስድስት ዓመት እስራት ተፈረደባት
አጭር መግለጫ
በሩሲያ እና በክራይሚያ ያሉት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የተዉት የታማኝነት ምሳሌ ያበረታታናል። የሰማዩ አባታችን ለመጽናት የሚያስፈልገንን ብርታት እንደሚሰጠን እንተማመናለን።—2 ተሰሎንቄ 1:4
a ቃለ መጠይቅ የተደረገላት ወደ እስር ቤት እንድትገባ ብይን ከመተላለፉ በፊት ነው።