በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት ታትያና ሱሺልኒኮቫ

ጥር 4, 2023 | የታደሰው፦ ኅዳር 17, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—እህታችን ተፈረደባት | ስደት ቢደርስባትም ሌሎችን ለመርዳት ቆርጣለች

ወቅታዊ መረጃ—እህታችን ተፈረደባት | ስደት ቢደርስባትም ሌሎችን ለመርዳት ቆርጣለች

ኅዳር 15, 2023 በኖቮኩዝኔትስክ የሚገኘው የኩዝኔትስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት እህት ታትያና ሱሺልኒኮቫ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን በማስተላለፍ የአራት ዓመት የገደብ እስራት ፈርዶባታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አትወርድም።

አጭር መግለጫ

እንደ ታትያና ሁሉ እኛም በይሖዋ እርዳታ ስደትን የተጋፈጡት “ታላቅ የምሥክሮች ደመና” የተዉትን ምሳሌ በመመርመር ብርታት እናገኛለን።—ዕብራውያን 12:1

የክሱ ሂደት

  1. ሰኔ 8, 2021

    የታጠቁ የፌዴራል ደህንነት አባላት በኖቮኩዝኔትስክ የሚገኙ ሦስት የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች በረበሩ። ታትያና እና ባለቤቷ ሰርጌ ለሦስት ሰዓት ምርመራ ተደረገባቸው

  2. ሰኔ 20, 2022

    ክስ ተመሠረተባት። ክሷ ‘ሃይማኖታዊ ውይይት አድርገሻል እንዲሁም በስብሰባዎች ላይ ተሳትፈሻል’ የሚል ነው

  3. ሐምሌ 22, 2022

    በይፋ ክስ ተመሠረተባት

  4. መስከረም 27, 2022

    ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ። ዳኛው፣ የአሠራር ጥሰት ተፈጽሟል በማለት ክሱ ወደ አቃቤ ሕግ እንዲመለስ አደረጉ

  5. ኅዳር 16, 2022

    ክሷ በድጋሚ መታየት ጀመረ