በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ግንቦት 12, 2021
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ | እህት ስቬትላና ሞኒስ ያቀረበችው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ

ወቅታዊ መረጃ | እህት ስቬትላና ሞኒስ ያቀረበችው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ

መጋቢት 9, 2022 የአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል ፍርድ ቤት እህት ስቬትላና ሞኒስ ጥፋተኛ ናት ተብሎ የተላለፈባትን ብይን ቀልብሷል። ጉዳይዋ በድጋሚ እንዲታይ በአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል ወደሚገኘው የቢሮቢድዣንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ይመራል።

ግንቦት 12, 2021 ሩሲያ ውስጥ የሚገኘው የአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል ፍርድ ቤት ስቬትላና ያቀረበችውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ አቃቤ ሕግ ያቀረበውን ጥያቄ በመቀበል በእህት ሞኒስ ላይ መጀመሪያ የተጣለባት የ10,000 ሩብል (135 የአሜሪካ ዶላር) መቀጫ ወደ ሁለት ዓመት ተኩል የገደብ እስር እንዲቀየር ወስኗል። እርግጥ እህት ሞኒስ አሁን ወህኒ አትወርድም።