ግንቦት 6, 2022 | የታደሰው፦ የካቲት 21, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—እህት ተፈረደባት | ታትያና ኦቢዤስትቪት በይሖዋ ታምናለች
የካቲት 20, 2023 በታታርስታን ሪፑብሊክ፣ በካዛን የሚገኘው የቫኪቶቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በእህት ታትያና ኦቢዤስትቪት ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ታትያና የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶባታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አትወርድም።
የክሱ ሂደት
ጥር 19, 2020
ባለሥልጣናት የታትያናን እና በካዛን የሚኖሩ ሌሎች የይሖዋ ምሥክሮችን ቤት ፈተሹ። ታትያና የወንጀል ምርመራ ከተደረገባት በኋላ ወደ ጊዜያዊ ማረፊያ ቤት ተወሰደች
ጥር 21, 2020
ከማረፊያ ቤት ተለቃ በቁም እስር እንድትቆይ ተደረገች
ግንቦት 25, 2021
ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
ታትያና በይሖዋ በመታመንና በገዛ ራሷ ማስተዋል ባለመመካት እንዲሁም በታማኝነት በመጽናት የተወችውን ምሳሌ እናደንቃለን።—ምሳሌ 3:5