ታኅሣሥ 21, 2021 | የታደሰው፦ ጥር 24, 2024
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—እህት ተፈረደባት | እህት ዬሌና ሜንቺኮቫ ታማኝ የአምላክ አገልጋዮች በተዉት ምሳሌ ላይ ማሰላሰሏና የቅርብ ወዳጇ ወደሆነው ወደ ይሖዋ መጸለይዋ አጠናክሯታል
ጥር 23, 2024 በካራቻዬቮ ቺርኬሲያ ሪፑብሊክ የሚገኘው የቺርክየስክ ከተማ ፍርድ ቤት እህት ዬሌና ሜንቺኮቫ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን ያስተላለፈ ሲሆን የአራት ዓመት ከስድስት ወር የገደብ እስራት ፈርዶባታል። አሁን ወህኒ አትወርድም።
ታኅሣሥ 5, 2022 አምስተኛው ጠቅላይ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት፣ በእህት ዬሌና ሜንቺኮቫ ላይ የተላለፈውን ብይን ቀለበሰ። ጉዳይዋ በድጋሚ እንዲታይ ወደ ታችኛው ፍርድ ቤት ይላካል።
የክሱ ሂደት
ታኅሣሥ 15, 2021
በካራቻዬቮ ቺርኬሲያ ሪፑብሊክ የሚገኘው የቺርክየስክ ከተማ ፍርድ ቤት ዬሌና ጥፋተኛ ናት የሚል ውሳኔ በማስተላለፍ በአምስት ዓመት የገደብ እስራት እንድትቀጣ ወሰነ
ሰኔ 9, 2021
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
መጋቢት 9, 2021
መርማሪው ለሁለተኛ ጊዜ ክስ የመሠረተባት ሲሆን ክሱ የተመሠረተው በጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴ ውስጥ ሌሎችን ለማካተት “የወንጀል ዕቅድ አውጥታለች” በሚል ነው
የካቲት 10, 2021
ዬሌና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በመጠቀም ሁኔታውን ለማስረዳት ብትሞክርም መርማሪው ዬሌና ክሱ እንዲሰረዝላት ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ አደረገ። እንዲያውም ዬሌና የተካፈለችባቸው እንቅስቃሴዎች “ወንጀል ነክ” እንደሆኑ የሚያረጋግጠው አንዱ ማስረጃ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን መጠቀሟ እንደሆነ ገለጸ
ኅዳር 13, 2020
መርማሪው ዬሌና መዝሙር በመዘመሯና ወደ ይሖዋ በመጸለይዋ የወንጀል ክስ መሠረተባት
ኅዳር 12, 2020
ባለሥልጣናት ለሁለተኛ ጊዜ የዬሌናን ቤት ፈተሹ
ታኅሣሥ 16, 2019
የቺርክየስክ የፌደራል ደህንነት ቢሮ አባላት የዬሌናን ጨምሮ የአሥር የይሖዋ ምሥክር ቤተሰቦችን ቤቶች ፈተሹ
አጭር መግለጫ
ይሖዋ እህት ዬሌናን ጨምሮ ስደትን እየተጋፈጡ ያሉ ታማኝ አገልጋዮቹን በሙሉ ማጽናናቱንና ማበረታታቱን እንዲቀጥል ጸሎታችን ነው።—መዝሙር 119:49, 50