በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት ጋሊና ኮሚሳሮቫ

ግንቦት 1, 2024 | የታደሰው፦ ሐምሌ 9, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—እህት ተፈረደባት | “ከዚህ የተለየ ሕይወት መኖር አልፈልግም”

ወቅታዊ መረጃ—እህት ተፈረደባት | “ከዚህ የተለየ ሕይወት መኖር አልፈልግም”

ሐምሌ 8, 2024 በሰማረ ክልል፣ በቶልያቲ ከተማ የሚገኘው የሴንትራልኒ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ እህት ጋሊና ኮሚሳሮቫ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን አስተላልፏል። የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶባታል። አሁን ወህኒ አትወርድም።

አጭር መግለጫ

እንደ ጋሊና ሁሉ እኛም ‘የይሖዋ እንደሆንን’ ስለምናውቅ እሱን የማወቅና የማገልገል መብታችንን ከፍ አድርገን እንመለከተዋለን።​—ሮም 14:8

የክሱ ሂደት

  1. መስከረም 7, 2023

    የክስ ፋይል ተከፈተባት

  2. መስከረም 8, 2023

    ቤቷ ተፈተሸ፤ ምርመራም ተደረገባት

  3. መስከረም 19, 2023

    የጉዞ ገደብ ተጣለባት

  4. ታኅሣሥ 18, 2023

    ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ