መስከረም 13, 2023 | የታደሰው፦ መጋቢት 12, 2024
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—እህት ተፈረደባት | “የይሖዋ ምሥክር በመሆኔ እኮራለሁ!”
መጋቢት 1, 2024 በኦርዮል ከተማ የሚገኘው የሶቪየትስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት እህት ታትያና ፒስካሬቫ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን በማስተላለፍ የሁለት ዓመት ከስድስት ወር የጉልበት ሥራ እንድትሠራ ፈርዶባታል። በማረሚያ ቤቱ ውስጥ እየኖረች በተመደበችበት ቦታ ማኅበራዊ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባታል።
አጭር መግለጫ
እንደ ታትያና ሁሉ እኛም በይሖዋ ስም እንደምንጠራና እሱ ፈጽሞ እንደማይለየን ማወቃችን ያበረታታናል እንዲሁም ያጽናናናል። ምሥክሮቹ ተብለን በመጠራታችን ክብር ይሰማናል።—ኢሳይያስ 44:8
የክሱ ሂደት
ታኅሣሥ 9, 2020
የታትያና እና የቭላድሚር ቤት ተፈተሸ። ቭላድሚር በቁጥጥር ሥር ዋለ
ታኅሣሥ 11, 2020
ቭላድሚር ወደ ማረፊያ ቤት ተላከ
ጥቅምት 28, 2021
በታትያና ላይ የክስ ፋይል ተከፈተባት
ሚያዝያ 10, 2023
ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ