መጋቢት 21, 2024 | የታደሰው፦ ሚያዝያ 12, 2024
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—እህት ተፈረደባት | “የይሖዋ እንክብካቤ ተቋርጦብን አያውቅም”
ሚያዝያ 12, 2024 በኬሜሮቮ ክልል በፕሮኮፕዬቭስክ የሚገኘው የሴንትራልኒ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ እህት ዬሌና ችዬርኒክ ጥፋተኛ ነች በማለት የሦስት ዓመት የገደብ እስራት በይኖባታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አትገባም።
አጭር መግለጫ
በጣም ከባድ በሆነ ፈተና ለማለፍ ብንገደድም እንኳ ይሖዋ ‘እንደማይለወጥ’ እንዲሁም ለመጽናት የሚያስፈልገንን “መልካም ስጦታ ሁሉና ፍጹም ገጸ በረከት ሁሉ” መስጠቱን እንደማያቋርጥ ማወቃችን ያጽናናናል።—ያዕቆብ 1:17
የክሱ ሂደት
ሐምሌ 12, 2020
ቤታቸው ተፈተሸ። ዬሌና እና ዩሪ ምርመራ ተደረገባቸው
ግንቦት 25, 2023
የወንጀል ክስ ተመሠረተባት
ነሐሴ 15, 2023
የጉዞ ክልከላዎች ተጣሉባት
ጥቅምት 9, 2023
ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ