ግንቦት 1, 2023 | የታደሰው፦ ነሐሴ 30, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—እህት ተፈረደባት | ‘ያጋጠሙኝ ችግሮች ጊዜያዊ ናቸው’
ነሐሴ 28, 2023 በካራቻዬቮ-ቺርኬሲያ የሚገኘው የኡሩፕስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በእህት ኢሪና ፔሬፊሌቫ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል፤ በአምስት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት እንድትቀጣም ወስኗል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አትወርድም።
አጭር መግለጫ
እንደ ኢሪና ሁሉ እኛም ፈተናዎች ሲያጋጥሙን አንድ እውነታ ማወቃችን ያጽናናናል፤ ይኸውም ፈተናው ምንም ያህል ከባድ ቢሆን ይሖዋ ለታማኝ አገልጋዮቹ ካዘጋጀላቸው በረከቶች ጋር ሲነጻጸር “ጊዜያዊና ቀላል” ነው።—2 ቆሮንቶስ 4:17
የክሱ ሂደት
ጥር 9, 2021
ቤቷ ተፈተሸ
ኅዳር 22, 2021
የክስ ፋይል ተከፈተባት
ኅዳር 23, 2021
ቤቷ እንደገና ተፈተሸ
ኅዳር 29, 2021
በጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴዎች ተሳትፈሻል የሚል ክስ ቀረበባት
ጥቅምት 15, 2022
የጉዞ ክልከላዎች ተጣሉባት
ታኅሣሥ 6, 2022
ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ