በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት ቫለንቲና ሳሙስ

ሐምሌ 26, 2023 | የታደሰው፦ ታኅሣሥ 20, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—እህት ተፈረደባት | ‘ይሖዋ ሁልጊዜ ከጎኔ ነው’

ወቅታዊ መረጃ—እህት ተፈረደባት | ‘ይሖዋ ሁልጊዜ ከጎኔ ነው’

ታኅሣሥ 19, 2023 በኮስትሮማ የሚገኘው የዲሚትሮቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ እህት ቫለንቲና ሳሙስ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን በማስተላለፍ በስድስት ዓመት የገደብ እስራት እንድትቀጣ ወስኗል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አትወርድም።

አጭር መግለጫ

በሚደርሱብን ፈተናዎች ሁሉ በይሖዋ መታመን እንደምንችል ማወቃችን ያጽናናናል፤ በእርግጥም “እንደ አምላካችን ያለ ዓለት የለም።”—1 ሳሙኤል 2:2

የክሱ ሂደት

  1. የካቲት 17, 2022

    የክስ ፋይል ተከፈተባት

  2. መጋቢት 15, 2022

    ቤቷ ተፈተሸ

  3. ታኅሣሥ 15, 2022

    የወንጀል ክስ ተመሠረተባት እንዲሁም የጉዞ እገዳ ተጣለባት

  4. መጋቢት 24, 2023

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ