በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት ኦልጋ ዤላቭስካያ

ጥር 17, 2023 | የታደሰው፦ ሚያዝያ 17, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—እህት ተፈረደባት | ‘ይሖዋ ከጎኔ አይለይም’

ወቅታዊ መረጃ—እህት ተፈረደባት | ‘ይሖዋ ከጎኔ አይለይም’

ሚያዝያ 17, 2023 በቼልያቢንስክ ክልል የሚገኘው የሚታለርጂቼስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ እህት ኦልጋ ዤላቭስካያ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን አስተላልፏል፤ የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶባታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አትወርድም።

አጭር መግለጫ

ስለ አንድ ነገር እርግጠኞች ነን፤ የይሖዋ አገልጋዮች የመጣው ቢመጣ እሱ ስለሚደግፋቸው ‘ፈጽሞ አይናወጡም።’—መዝሙር 16:8

የክሱ ሂደት

  1. ሰኔ 16, 2018

    ፖሊሶች የኦልጋ ቤት ውስጥ የድምፅና የቪዲዮ ክትትል መሣሪያ ገጠሙ፤ እንቅስቃሴዎቿን መከታተል ጀመሩ

  2. መጋቢት 26, 2019

    ከወንድም ቭላድሚር ሱቮሮቭ ምርመራ ጋር በተያያዘ ቤቷ ተፈተሸ

  3. ነሐሴ 31, 2021

    የወንጀል ክስ ተመሠረተባት። ቤትሽን ለስብሰባ በመፍቀድ የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴ ደግፈሻል ተብላ ተከሰሰች

  4. ጥቅምት 22, 2021

    ስትሮክ አጋጥሟት ሐኪም ቤት ተኛች

  5. መስከረም 28, 2022

    ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ