ታኅሣሥ 13, 2021 | የታደሰው፦ ሰኔ 13, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—እህት ተፈረደባት | “ደስተኛ ያደረገኝ የይሖዋ የቅርብ ወዳጅ መሆኔ . . . ነው”
ሰኔ 6, 2023 በፕሪሞርይስ ክልል የሚገኘው የፓርቲዛንስክ ከተማ ፍርድ ቤት፣ እህት አይሪና ቡግላክ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን አስተላልፏል፤ የሁለት ዓመት ከስድስት ወር የገደብ እስራት ተፈርዶባታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አትወርድም።
የክሱ ሂደት
ነሐሴ 6, 2021
የአይሪና ጉዳይ ወደ ፓርቲዛንስክ ከተማ ፍርድ ቤት ተመለሰ
ኅዳር 30, 2020
ምንም ማስረጃ ማግኘት ስላልተቻለ የአይሪና ጉዳይ ወደ አቃቤ ሕጉ ቢሮ ተመለሰ
ጥር 31, 2020
ከ107 ቀን በኋላ ከቁም እስር ነፃ ሆነች
ጥቅምት 16, 2019
አይሪና 179 ቀናት በእስር ካሳለፈች በኋላ ከማረፊያ ቤት ወጥታ በቁም እስር እንድትቆይ ተደረገች
ሚያዝያ 20, 2019
የፌደራል ደህንነት ቢሮ አባላት ከሌሊቱ 9:00 ላይ የአይሪናን ቤት ፈተሹ። የደህንነት አባላቱ ሃይማኖታዊ ስብሰባዎችን በማደራጀትና በመምራት ወንጀል ከሰሷት። ከዚያም ወደ ማረፊያ ቤት የተወሰደች ሲሆን የምትወጣበት ጊዜ ሦስት ጊዜ ተራዝሟል
ሚያዝያ 19, 2019
ስምንት የፌደራል ደህንነት ቢሮ አባላት የ80 ዓመት አረጋዊ የሆኑትን የእህት ኔሊ ታራስዩክን ቤት በኃይል ሰብረው በመግባት ፈተሹ። አይሪና እና ልጇ ናታልያ በወቅቱ እህት ኔሊ ቤት ከነበሩት በርካታ እህቶች መካከል ነበሩ። የደህንነት አባላቱ ፍተሻውን እያካሄዱ ሳለ እህት ኔሊ ታመው ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ። የቀሩት እህቶች ታስረው ምሽቱን ሙሉ ምርመራ ተደረገባቸው። አይሪና በቁጥጥር ሥር እንድትቆይ ተደረገች
አጭር መግለጫ
ይሖዋ እህት አይሪናንም ሆነ በሩሲያ ያሉ ውድ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን በትዕግሥትና በደስታ እንዲጸኑ እንዲረዳቸው ሁሌም እንጸልያለን።—ቆላስይስ 1:11