በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት ኢሪና ሚኻይሌንኮ

ታኅሣሥ 9, 2022 | የታደሰው፦ ሚያዝያ 25, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—እህት የገንዘብ መቀጮ ተበየነባት | “አጥብቆ መጸለይ ይረዳኛል”

ወቅታዊ መረጃ—እህት የገንዘብ መቀጮ ተበየነባት | “አጥብቆ መጸለይ ይረዳኛል”

ሚያዝያ 25, 2023 በቼልያቢንስክ ከተማ የሚገኘው የሜታለርጂቼስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ እህት ኢሪና ሚኻይሌንኮ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን አስተላልፏል። የ120,000 ሩብል (1,471 የአሜሪካ ዶላር) መቀጮ ተበይኖባታል።

አጭር መግለጫ

የኢሪና ቅንዓትና በይሖዋ ላይ ያላት እምነት የሚያበረታታ ነው፤ እንዲህ የታመነችበት ይሖዋ “የታማኝ አገልጋዮቹን ሕይወት [የሚጠብቅ]” አምላክ ነው።—መዝሙር 97:10

የክሱ ሂደት

  1. መጋቢት 26, 2019

    በቼልያቢንስክ አካባቢ በሚኖሩ አሥር የይሖዋ ምሥክሮች ቤተሰቦች መኖሪያ ላይ ፍተሻ ተካሄደ፤ የኢሪና ቤትም ተፈተሸ

  2. ነሐሴ 31, 2021

    የወንጀል ክስ ተመሠረተባት

  3. ጥቅምት 22, 2021

    ቤቷ እንደገና ተፈተሸ። ለምርመራ ተወሰደች። የጉዞ እገዳም ተጣለባት

  4. ጥቅምት 27, 2021

    በታገደ ሃይማኖታዊ ድርጅት እንቅስቃሴዎች ተሳትፋለች የሚል ክስ በይፋ ተመሠረተባት

  5. መስከረም 7, 2022

    ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ