በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በኬሜሮቮ ክልል፣ በኖቮኩዝኔትስክ የሚገኘው የኩዝንዬትስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት

የካቲት 20, 2023| የታደሰው፦ ሐምሌ 14, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—እህቶች ተፈረደባቸው | “ልወጣው የማልችለው አንድም ችግር የለም”

ወቅታዊ መረጃ—እህቶች ተፈረደባቸው | “ልወጣው የማልችለው አንድም ችግር የለም”

ሐምሌ 11, 2023 በኖቮኩዝኔትስክ የሚገኘው የኩዝንዬትስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ እህት ልዩቦቭ ሴሬብርያኮቫ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን አስተላልፏል፤ የአራት ዓመት የገደብ እስራት ተበይኖባታል። አሁን ወህኒ አትወርድም።

አጭር መግለጫ

ልዩቦቭ፣ ይሖዋ ‘ለእሷ ሲል እርምጃ እንደሚወስድ’ ያላት ጠንካራ እምነት እኛም ተመሳሳይ ፈተናዎች ሲያጋጥሙን ግሩም ምሳሌ ይሆነናል።—መዝሙር 37:5

የክሱ ሂደት

  1. ኅዳር 2019-2020

    በኖቮኩዝኔትስክ የሚኖሩ አንዳንድ የይሖዋ ምሥክሮች በድምፅና በቪዲዮ ክትትል ተደረገባቸው

  2. ሐምሌ 8, 2022

    ልዩቦቭ በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባዎች ላይ ተገኝታለች እንዲሁም ከሌሎች ጋር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ውይይት አድርጋለች በሚል የወንጀል ምርመራ ይደረግባት ጀመር

  3. ሐምሌ 26, 2022

    በጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴዎች ተካፍላለች የሚል ክስ ተመሠረተባት። የጉዞ ክልከላዎች ተጣሉባት

  4. መስከረም 21, 2022

    ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

a ይህ ዜና በተጠናቀረበት ወቅት የእህት ልዩቦቭን ፎቶግራፍ ማግኘት አልተቻለም።