በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ እህት ማርጋሪታ ሞይሴዬንኮ እና ባለቤቷ ኮንስታንቲን፣ እህት ጋሊና ያትሲክ እና እህት የሌና ያትሲክ

መስከረም 14, 2023 | የታደሰው፦ መስከረም 22, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—እህቶች ተፈረደባቸው | ሦስት እህቶች በጸሎት ብርታት አግኝተዋል

ወቅታዊ መረጃ—እህቶች ተፈረደባቸው | ሦስት እህቶች በጸሎት ብርታት አግኝተዋል

መስከረም 21, 2023 በአሙር ክልል የሚገኘው የዜያ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በእህት ማርጋሪታ ሞይሴዬንኮ ላይ የሦስት ዓመት፣ በእህት ጋሊና ያትሲክ ላይ የሁለት ዓመት እዲሁም በእህት የሌና ያትሲክ ላይ የሁለት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት ፈረደባቸው። አሁን ወህኒ አይወርዱም።

አጭር መግለጫ

የእህቶቻችን ተሞክሮ፣ ይሖዋ ጸሎታችንን እንደሚሰማና ማንኛውንም መከራ ለመቋቋም የሚያስችሉንን ባሕርያት እንድናዳብር እንደሚረዳን ያስታውሰናል።—1 ዮሐንስ 5:14

የክሱ ሂደት

  1. መጋቢት 21, 2019

    የእነማርጋሪታ ቤት ተፈተሸ

  2. ጥቅምት 13, 2020

    የየሌና እና የጋሊና ቤቶች ተፈተሹ

  3. ኅዳር 22, 2021

    የክስ ፋይል ተከፈተባቸው

  4. የካቲት 15, 2022

    የጉዞ ገደብ ተጣለባቸው

  5. ሚያዝያ 24, 2023

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

a b እህት ጋሊና ያትሲክ እና የሌና ያትሲክ የሥጋ ዝምድና የላቸውም