በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ኮንስታንቲን ሳኒኮቭ

ሚያዝያ 8, 2022 | የታደሰው፦ የካቲት 16, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—እስራት ተፈረደበት | ማረፊያ ቤት ያለ አንድ አባት ቤተሰቡን በመንፈሳዊ መንከባከቡን ቀጥሏል

ወቅታዊ መረጃ—እስራት ተፈረደበት | ማረፊያ ቤት ያለ አንድ አባት ቤተሰቡን በመንፈሳዊ መንከባከቡን ቀጥሏል

የካቲት 15, 2023 በካዛን የሚገኘው የሶቬትስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ኮንስታንቲን ሳኒኮቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል፤ የስድስት ዓመት ተኩል እስራትም ፈርዶበታል። ከነሐሴ 2020 ጀምሮ ማረፊያ ቤት የቆየ ሲሆን አሁንም እንደታሰረ ነው።

የክሱ ሂደት

  1. ነሐሴ 25, 2020

    መርማሪዎች በኮንስታንቲን ቤት ውስጥ የድምፅ ማስተላለፊያ መሣሪያዎችን በድብቅ ካስቀመጡ በኋላ የወንጀል ክስ ተመሠረተበት። ባለሥልጣናቱ፣ ኮንስታንቲን የመጽሐፍ ቅዱስ ውይይቶችን መምራቱን የጽንፈኝነት እንቅስቃሴዎችን እንደ ማደራጀት ቆጠሩት

  2. ነሐሴ 27, 2020

    በቁጥጥር ሥር ውሎ ወዲያውኑ ማረፊያ ቤት ገባ

  3. ግንቦት 26, 2021

    ፍርድ ቤቱ፣ ባለቤቱ መጥታ እንዳትጠይቀው አገዳት፤ እስካሁንም እሱን ለመጠየቅ ያቀረበቻቸውን ጥያቄዎች ውድቅ ማድረጉን ቀጥሏል

  4. ነሐሴ 20, 2021

    ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ኮንስታንቲን እስር ላይ ቢሆንም ቤተሰቡን በመንፈሳዊ መንከባከቡን ቀጥሏል። ይሖዋም ‘የራሱ የሆኑትን’ ምንጊዜም እንደሚንከባከብ እርግጠኞች ነን።—1 ጢሞቴዎስ 5:8

a ወንድም ሳኒኮቭ በአሁኑ ወቅት ማረፊያ ቤት ይገኛል፤ በመሆኑም የእሱን ሐሳብ መጠየቅ አልቻልንም።