መስከረም 9, 2022| የታደሰው፦ መጋቢት 20, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—እስራት ተፈረደበት | “ደስታዬ . . . ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ተቀጣጥሏል”
መጋቢት 17, 2023 በክራስናያርስክ ክልል የሚገኘው የሶስኖቮቦርስክ ከተማ ፍርድ ቤት በወንድም ዩሪ ያኮቭሌቭ ላይ ብይን አስተላልፏል፤ ወንድም ዩሪ የስድስት ዓመት ከሁለት ወር እስራት ተፈርዶበታል። ከመጋቢት 2022 ጀምሮ ማረፊያ ቤት የቆየ ሲሆን አሁንም እንደታሰረ ነው።
የክሱ ሂደት
ከሰኔ እስከ ታኅሣሥ 2021
ባለሥልጣናቱ የዩሪን ስልክ ጠለፉ፤ እንዲሁም በሌሎች መንገዶች ሲከታተሉት ቆዩ
መጋቢት 28, 2022
የወንጀል ክስ ተመሠረተበት። አንድ ጽንፈኛ ድርጅት በቪዲዮ ኮንፈረንስ የሚያደርገውን ስብሰባ አደራጅቷል በሚል ተከሰሰ። መርማሪው ያለማዘዣ የዩሪን ቤት ፈተሸ
መጋቢት 29, 2022
የአምስት ሌሎች የይሖዋ ምሥክር ቤተሰቦች እንዲሁም ከዩሪ ጋር መጽሐፍ ቅዱስን የሚወያይ አንድ ሰው ቤት ተፈተሸ። ዩሪ በቁጥጥር ሥር ውሎ ወደ ጣቢያ ተወሰደ
መጋቢት 30, 2022
ማረፊያ ቤት ተላከ
ሰኔ 20, 2022
ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
ይሖዋ ተስፋ የሚያደርጉበትን ታማኝ አገልጋዮቹን መደገፉንና ለእነሱ ኃይል መስጠቱን እንደሚቀጥል እርግጠኞች ነን።—ኢሳይያስ 40:31