ግንቦት 6, 2024 | የታደሰው፦ ሐምሌ 11, 2024
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—እስራት ተፈረደባቸው | ‘ከይሖዋ ቁጥጥር ውጭ የሆነ ምንም ነገር የለም’
ሐምሌ 10, 2024 በፕሪሞርይስ ግዛት የሚገኘው የኮሮልስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ቦሪስ አንድሬቭ፣ ወንድም አናቶሊ ሊ እና እህት ናታሊያ ሻራፖቫ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ቦሪስ የስድስት ዓመት፣ አናቶሊ የስድስት ዓመት ከስድስት ወር፣ ናታሊያ ደግሞ የሦስት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል። ሦስቱም በአሁኑ ወቅት ማረፊያ ቤት ሲሆኑ በዚያው እስራታቸውን ይቀጥላሉ።
አጭር መግለጫ
ይሖዋ ለቦሪስ፣ ለናታሊያ እና ለአናቶሊ እንዳደረገው ሁሉ በጭንቀት ቀን እንደሚሰማንና ለመጽናት የሚያስችል ጥንካሬ እንደሚሰጠን እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 20:1
የክሱ ሂደት
ሐምሌ 28, 2022
የክስ ፋይል ተከፈተባቸው
ጥቅምት 6, 2022
ያሮስላቭስኪ መንደር ውስጥ አሥራ ሁለት ቤቶች ተፈተሹ። ቦሪስ እና ናታሊያ ጣቢያ ተወሰዱ
ጥቅምት 7, 2022
ቦሪስ እና ናታሊያ ማረፊያ ቤት ተላኩ
ጥቅምት 12, 2022
አናቶሊ ጣቢያ እንዲያድር ተደረገ
ጥቅምት 13, 2022
አናቶሊ ማረፊያ ቤት ገባ
ጥቅምት 5, 2023
ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ