በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አንድሬ ዡኮቭ

ሰኔ 7, 2022| የታደሰው፦ ኅዳር 21, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ከክስ ነፃ እንዲሆን የተላለፈው ብይን ተቀለበሰ | ይሖዋ እንደሚወደውና እንደሚደግፈው እርግጠኛ ሆኗል

ወቅታዊ መረጃ—ከክስ ነፃ እንዲሆን የተላለፈው ብይን ተቀለበሰ | ይሖዋ እንደሚወደውና እንደሚደግፈው እርግጠኛ ሆኗል

ኅዳር 20, 2023 በሃንቲ ማንሲስክ ራስ ገዝ ክልል—ዩግራ የሚገኘው ፍርድ ቤት ወንድም አንድሬ ዡኮቭ ከቀረበበት ክስ ነፃ እንዲሆን ያስተላለፈውን ብይን ቀልብሶታል። ክሱ በድጋሚ በፍርድ ቤት ይታያል።

ነሐሴ 7, 2023 በክሃንቲ ማንሲስ ራስ ገዝ ክልል—ዩግራ የሚገኘው የዩጎርስኪ የአውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም አንድሬ ዡኮቭን ከቀረበበት ክስ ነፃ አድርጎታል። ፍርድ ቤቱ፣ በቀረቡበት በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ እንዳልሆነ በይኗል።

የክሱ ሂደት

  1. ነሐሴ 17, 2020

    በአንድሬ ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተ፤ “የጽንፈኛ” ድርጅት ሚስጥራዊ ስብሰባዎችን መርቷል በሚል ነው የተከሰሰው

  2. ነሐሴ 19, 2020

    የአንድሬን ጨምሮ ዘጠኝ የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ተበረበሩ። አንድሬ ማረፊያ ቤት እንዲቆይ ተደረገ

  3. ነሐሴ 20, 2020

    በዋስትና ተለቀቀ

  4. ጥር 14, 2021

    ስሙ በጽንፈኞች ዝርዝር ውስጥ ተካተተ፤ የባንክ ሒሳቡ ታገደበት

  5. ነሐሴ 4, 2021

    ባለሥልጣናቱ አንድሬ “ለይሖዋ አምላክ ጸልዮአል፣ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት አካሂዷል እንዲሁም ሃይማኖታዊ ጽሑፎችን አንብቧል” የሚሉና ሌሎችም ተጨማሪ ክሶች መሠረቱበት። ከዚያም የወንጀል ምርመራ ተደረገበት

  6. ጥቅምት 15, 2021

    በአንድሬ ላይ የተመሠረተው የወንጀለኛ ክስ እንዲሰረዝ የቀረበው አቤቱታ ውድቅ ተደረገ

  7. ታኅሣሥ 29, 2021

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ይሖዋ ለአንድሬም ሆነ ስደትን በጽናት እየተቋቋሙ ላሉ ለሁሉም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እያደረገላቸው ያለው ድጋፍ ‘ለጥሩነቱ ማስረጃ’ ነው፤ ‘ረዳትና አጽናኝ’ እንደሆነም ያረጋግጣል።—መዝሙር 86:17 የግርጌ ማስታወሻ