በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አንድሬ ኦካፕኪን እና ባለቤቱ ኢሪና

ሚያዝያ 20, 2023 | የታደሰው፦ ነሐሴ 14, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም መቀጮ ተጣለበት | ወንድም ኦካፕኪን የፍጥረት ሥራዎችን መመልከቱ አበርትቶታል

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም መቀጮ ተጣለበት | ወንድም ኦካፕኪን የፍጥረት ሥራዎችን መመልከቱ አበርትቶታል

ነሐሴ 13, 2024, በኢቫኖቮ ክልል የሚገኘው የኪንሸምስኪ ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም አንድሬ ኦካፕኪን ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል።የ540,000 ሩብል (6,064 የአሜሪካ ዶላር) መቀጮ ተጥሎበታል።

አጭር መግለጫ

እንደ አንድሬ ሁሉ እኛም “የአምላክን ድንቅ ሥራዎች” እናደንቃለን፤ የይሖዋን ፍቅራዊ አሳቢነት እንድናስታውስ ይረዱናል።—ኢዮብ 37:14

የክሱ ሂደት

  1. ኅዳር 18, 2021

    በአንድሬ ላይ የክስ ፋይል ተከፈተ

  2. ኅዳር 23, 2021

    የአንድሬን ጨምሮ የስድስት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ተፈተሹ። አንድሬ በቁጥጥር ሥር ውሎ ጣቢያ እንዲያድር ተደረገ

  3. ኅዳር 24, 2021

    የወንጀል ክስ ተመሠረተበት

  4. ኅዳር 25, 2021

    ማረፊያ ቤት እንዲወርድ ተደረገ

  5. የካቲት 17, 2022

    ከማረፊያ ቤት ተለቀቀ፤ የቁም እስረኛ ተደረገ

  6. ሐምሌ 14, 2022

    ከቁም እስር ነፃ ሆነ፤ የጉዞ እገዳ ተጣለበት

  7. ታኅሣሥ 15, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ