በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አናቶሊ ኢሳኮቭ እና ባለቤቱ ታቲያና

ጥር 1, 2024| የታደሰው፦ ነሐሴ 9, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም መቀጮ ተጣለበት | ‘ይሖዋ ፈጽሞ አልተወኝም’

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም መቀጮ ተጣለበት | ‘ይሖዋ ፈጽሞ አልተወኝም’

ነሐሴ 8, 2024 በኩርጋን ክልል የሚገኘው የኩርጋን ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም አናቶሊ ኢሳኮቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል። አናቶሊ የ400,000 ሩብል (4,522 የአሜሪካ ዶላር) መቀጮ ተጥሎበታል። አሁን ወህኒ አይወርድም።

አጭር መግለጫ

አናቶሊ ብዙ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ቢኖሩበትም በቆራጥነትና በታማኝነት ረገድ የተወውን ምሳሌ እናደንቃለን። ደግሞም ምንም ዓይነት ፈተና ቢያጋጥመን ይሖዋ ‘የልባችን ዓለት’ እንደሚሆን ማወቃችን ያስደስተናል።​—መዝሙር 73:26

የክሱ ሂደት

  1. ሐምሌ 13, 2021

    የወንጀል ክስ ተመሠረተ

  2. ሐምሌ 14, 2021

    ቤቱ ተፈተሸ። ወደ ጊዜያዊ ማረፊያ ጣቢያ እንዲገባ ተደረገ

  3. ሐምሌ 15, 2021

    ወደ ማረፊያ ቤት እንዲዛወር ተደረገ

  4. ሐምሌ 21, 2021

    አናቶሊ ከማረፊያ ቤት ወጥቶ የኬሞቴራፒ ሕክምናውን እንዲቀጥል ለኩርጋን ክልል የጤና ክፍል ጥያቄ ቀረበ

  5. ነሐሴ 28, 2021

    የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ከማረፊያ ቤት ተለቀቀ። ሆኖም የጉዞ ገደብ ተጣለበት

  6. ሐምሌ 6, 2023

    ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ