በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ሰርጌ ሜልኒኮቭ

መጋቢት 25, 2021
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ | ወንድም ሰርጌ ሜልኒኮቭ በእምነቱ ምክንያት በቁጥጥር ሥር በቆየበት ወቅት ይሖዋ ‘ከሰብዓዊ ኃይል በላይ የሆነውን ኃይል’ እንደሰጠው ተናገረ

ወቅታዊ መረጃ | ወንድም ሰርጌ ሜልኒኮቭ በእምነቱ ምክንያት በቁጥጥር ሥር በቆየበት ወቅት ይሖዋ ‘ከሰብዓዊ ኃይል በላይ የሆነውን ኃይል’ እንደሰጠው ተናገረ

ግንቦት 12, 2022 የፕሪሞርይስ ክልላዊ ፍርድ ቤት ወንድም ሰርጌ ሜልኒኮቭ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። እርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።

የካቲት 3, 2022 በፕሪሞርይስ ክልል የሚገኘው የኡሱሪስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ሰርጌ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላለፈ። የሦስት ዓመት የገደብ እስራት ተበይኖበታል።

አጭር መግለጫ

ሰርጌ ሜልኒኮቭ

  • የትውልድ ዘመን፦ 1973 (ታዬርንዪ፣ ፕሪሞርይስ ክልል)

  • ግለ ታሪክ፦ አናጺ፣ የእሳት አደጋ ሠራተኛ፣ ዓሣ አጥማጅና የጽዳት ሠራተኛ ሆኖ ሠርቷል። ወጣት እያለ ሆኪ እና መረብ ኳስ መጫወት ይወድ ነበር። ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ማጥናት የጀመረው በ2000 መጀመሪያ አካባቢ ነው። በ2003 ወደ ኡሱሪስኪ ተዛወረ፤ በዚያው ዓመት መጨረሻ ላይ ተጠመቀ

የክሱ ሂደት

በወንድም ሰርጌ ሜልኒኮቭ ላይ የወንጀል ክስ የተመሠረተው ሰኔ 2019 ነው። ባለሥልጣናቱ ወንድም ሰርጌን የያዙት ለመጽሐፍ ቅዱስ ፍላጎት ካሳየ ሰው ጋር ሲወያይ ነው። ባለሥልጣናቱ ቤቱን የፈተሹ ከመሆኑም ሌላ ላፕቶፕ ኮምፒውተሩን እና ስልኩን ወርሰውበታል።

ሰርጌ አራት ወራት በማረፊያ ቤት እንዲሁም 145 ቀናት በቁም እስር አሳልፏል። ሰርጌ ሁኔታው ከአቅሙ በላይ እንደሆነ የተሰማው ጊዜ ነበር። በዚህ ጊዜ በ1 ቆሮንቶስ 10:13 ላይ ያሰላስል ነበር፤ ይህም ወዲያው እንዲረጋጋ አድርጎታል። እንዲህ ብሏል፦ “ይሖዋ ይህ መከራ እንዲደርስብኝ መፍቀዱ መከራውን ልቋቋመው እንደምችል እርግጠኛ እንድሆን አድርጎኛል። ይሖዋ ‘ከሰብዓዊ ኃይል በላይ የሆነ ኃይል’ ሰጥቶኛል።”—2 ቆሮንቶስ 4:7

የካቲት 25, 2020 ሰርጌ ከቁም እስር ተለቀቀ። ሆኖም የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎበታል።

የፍርዱ ቤቱን ውሳኔ በምንጠባበቅበት በዚህ ጊዜ ይሖዋ ለሰርጌ እንዲሁም በሩሲያ ላሉ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በሙሉ ‘ረዳትና ጋሻ’ እንደሚሆንላቸው እንተማመናለን።—መዝሙር 115:11