በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ሰርጌ ቤሉሶቭ

ሚያዝያ 1, 2022
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ | ወንድም ሰርጌ ቤሉሶቭ ለአምላክ ስም ጥብቅና ቆሟል

ወቅታዊ መረጃ | ወንድም ሰርጌ ቤሉሶቭ ለአምላክ ስም ጥብቅና ቆሟል

ሰኔ 30, 2022 የቶምስክ ክልላዊ ፍርድ ቤት ወንድም ሰርጌ ቤሉሶቭ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አድርጓል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።

ሚያዝያ 14, 2022 በቶምስክ ክልል የሚገኘው የሴቬርስኪ ከተማ ፍርድ ቤት፣ ሰርጌ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን ያስተላለፈ ሲሆን የሦስት ዓመት የገደብ እስራት ፈርዶበታል።

የክሱ ሂደት

  1. ሐምሌ 14, 2020

    የፌዴራል ደህንነት አባላት፣ የሰርጌን ጨምሮ የሰባት የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች በረበሩ። ከብርበራው በፊት ባሉት ወራት፣ አንድ የመንግሥት ሰላይ መጽሐፍ ቅዱስን የመማር ፍላጎት ያለው መስሎ በመቅረብ የይሖዋ ምሥክሮቹ የሚያደርጓቸውን ስብሰባዎች ይቀርጽ ነበር

  2. መጋቢት 25, 2021

    በሰርጌ ላይ የክስ ፋይል ተከፈተ

  3. መጋቢት 30, 2021

    ሰላዩ የቀረጸውን ስብሰባ ማስረጃ በማድረግ በሰርጌ ላይ ክስ ተመሠረተበት። ሰርጌ የተከሰሰው በኢንተርኔት የቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት በሃይማኖታዊ ፕሮግራም ላይ በመካፈሉ፣ በፕሮግራሙ ላይም በመዘመሩና ለይሖዋ አምላክ በመጸለዩ ነው

አጭር መግለጫ

እንደ ሰርጌ የይሖዋን ስም የሚያወድሱ ሁሉ እሱ ‘የሕዝቡን ብርታት ከፍ እንደሚያደርግ’ እርግጠኞች ናቸው።—መዝሙር 148:13, 14