ጥቅምት 5, 2021
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ | ወንድም ቪታሊ ኦሜልቼንኮ ያገኘው ማበረታቻ ስደትን ለመቋቋም ረድቶታል
መስከረም 22, 2022 በሙርማንስክ ክልል የሚገኘው የኦክትያቢርስኪ የአውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ቪታሊ ኦሜልቼንኮን ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል። የ580,000 ሩብል (9,526 የአሜሪካ ዶላር) ቅጣት ተበይኖበታል።
የክሱ ሂደት
ጥር 29, 2021
የቪታሊ ክስ ወደ ፍርድ ቤት ተመራ
ጥር 20, 2020
ሕግ አስከባሪ አካላት ለምርመራ በቁጥጥር ሥር አዋሉት። ለሁለት ቀን ጣቢያ ከቆየ በኋላ ተለቀቀ። በክሱ ውስጥ ከተካተቱ ሰዎች ጋር እንዳይነጋገርና ኢንተርኔት እንዳይጠቀም ታገደ
ታኅሣሥ 23, 2019
በሙርማንስክ ክልል የሚገኘው የሩሲያ ፌዴሬሽን የምርመራ ኮሚቴ በቪታሊ ላይ የወንጀል ክስ መሠረተ። የተከሰሰው በቤቱ ሆኖ በይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች በመካፈሉ ምክንያት ነው
አጭር መግለጫ
ቪታሊ ከቅዱሳን መጻሕፍት ትምህርትና መጽናኛ ማግኘቱን ቀጥሏል፤ እኛም እሱ የተወው ምሳሌ ያበረታታናል።—ሮም 15:4