በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ቫሲሊ ሜሌሽኮ

ነሐሴ 17, 2021
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ | ወንድም ቫሲሊ ሜሌሽኮ በክራስኖዳር ክልል ጉዳያቸው በችኮላ ታይቶ ከተፈረደባቸው የይሖዋ ምሥክሮች አራተኛው ሆነ

ወቅታዊ መረጃ | ወንድም ቫሲሊ ሜሌሽኮ በክራስኖዳር ክልል ጉዳያቸው በችኮላ ታይቶ ከተፈረደባቸው የይሖዋ ምሥክሮች አራተኛው ሆነ

ሰኔ 14, 2022 አራተኛው ጠቅላይ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ወንድም ቫሲሊ ሜሌሽኮ ለሁለተኛ ጊዜ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። ቫሲሊ በእምነቱ ምክንያት አሁንም እንደታሰረ ነው።

የክሱ ሂደት

  1. ጥቅምት 7, 202 1 የክራስኖዳር ክልል ፍርድ ቤት ወንድም ቫሲሊ ሜሌሽኮ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። ቀደም ሲል የተላለፈበት ፍርድ በዚያው ይጸናል

  2. ነሐሴ 11, 2021

    በክራስኖዳር ክልል የሚገኘው የአብንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ የቫሲሊን ጉዳይ ለሁለት ቀናት ካየ በኋላ ጥፋተኛ ነው በማለት የሦስት ዓመት እስራት ፈርዶበታል። ወንድም ቫሲሊ ሜሌሽኮ ከፍርድ ቤት በቀጥታ ወደ እስር ቤት ተወስዷል። ቫሲሊ በዚህ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው በችኮላ ታይቶ ከተፈረደባቸው የይሖዋ ምሥክሮች አራተኛው ሆኗል a

  3. ነሐሴ 10, 2021

    የቫሲሊ ጉዳይ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ። ዳኛው ሲጠይቁት፣ ቫሲሊ ቀናተኛ የይሖዋ ምሥክር መሆኑን በድፍረት ተናገረ

  4. ሰኔ 24, 2021

    ቫሲሊ ቀደም ሲል ከወንድም አሌክሳንደር ኢቨሺን ጋር ያደረጋቸው ውይይቶች በተከሰሰባቸው ወንጀሎች ውስጥ ተካተቱ። አቃቤ ሕጉ “ከይሖዋ አምላክ አገልግሎት” ጋር በተያያዙ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ እንደተወያዩ ገልጿል

  5. ሚያዝያ 12, 2021

    ቫሲሊ “በሃይማኖታዊ ጽሑፎች ላይ የተመሠረቱ ንግግሮችን በማቅረቡና በመስማቱ፣” “በሃይማኖታዊ መጻሕፍት ላይ የቡድን ውይይት በማድረጉ” እንዲሁም በሌሎች እንቅስቃሴዎች በመካፈሉ ክስ ተመሠረተበት

  6. ሚያዝያ 7, 2021

    ማለዳ 12:30 ላይ ሦስት የታጠቁ የደህንነት አባላት፣ አራት መርማሪ ፖሊሶች እንዲሁም ሁለት ባለሥልጣናት የቫሲሊን እና የዞያን ቤት በግድ ፈተሹ። በኋላም ቫሲሊ ለምርመራ ተወሰደ። ከዚያም መርማሪዎቹ ከቤቱ ፊት ለፊት እንዲሁም ወንድሞች ቀደም ሲል ለአምልኮ ከሚሰበሰቡበት ሕንፃ ፊት ለፊት ፎቶግራፍ አነሱት። መርማሪዎቹ እነዚህን ፎቶግራፎች ያነሱት ወንጀል እንደፈጸመ የሚያሳይ ማስረጃ አድርገው ሊጠቀሙባቸው ነው። ቫሲሊ አካባቢውን ለቆ እንዳይሄድ ታዘዘ

አጭር መግለጫ

የፍርድ ሂደቱ በችኮላ መካሄዱና በሩሲያ በሚኖሩ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የሚደርሰው ስደት መቀጠሉ “ክፉ ወሬ” ቢሆንም ቫሲሊና ቤተሰቡ ‘በይሖዋ በመተማመን’ ጽኑ እንደሚሆኑና እንደማይናወጡ እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 112:7, 8

a ወንድም ኦሌግ ዳኒሎቭ መጋቢት 30, 2021 የሦስት ዓመት እስራት ተፈርዶበታል። ወንድም አሌክሳንደር ኢቨሺን የካቲት 10, 2021 የሰባት ዓመት ተኩል እስራት ተፈርዶበታል። ወንድም አሌክሳንደር ሽቼርቢና ደግሞ ሚያዝያ 6, 2021 የሦስት ዓመት እስራት ተፈርዶበታል።