በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም ቭላዲሚር ቼስኖኮቭ፣ ወንድም ቭላዲሚር ዱትኪን እና ወንድም ቫለሪ ያኮቭሌቭ

ጥር 7, 2022
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ | ወንድም ቭላዲሚር ቼስኖኮቭ፣ ወንድም ቭላዲሚር ዱትኪን እና ወንድም ቫለሪ ያኮቭሌቭ በእምነታቸው ምክንያት ፍርድ ቤት ቀረቡ

ወቅታዊ መረጃ | ወንድም ቭላዲሚር ቼስኖኮቭ፣ ወንድም ቭላዲሚር ዱትኪን እና ወንድም ቫለሪ ያኮቭሌቭ በእምነታቸው ምክንያት ፍርድ ቤት ቀረቡ

ሚያዝያ 13, 2022 የቹቫሽ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንድም ቭላዲሚር ቼስኖኮቭ፣ ወንድም ቭላዲሚር ዱትኪን እና ወንድም ቫለሪ ያኮቭሌቭ ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። በመሆኑም የተጣለባቸው ቅጣት ተፈጻሚ ይሆናል።

የካቲት 10, 2022 በቼቦክሳሪ የሚገኘው የካሊኒንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት በወንድም ቭላዲሚር ቼስኖኮቭ፣ በወንድም ቭላዲሚር ዱትኪን እና በወንድም ቫለሪ ያኮቭሌቭ ላይ ፍርድ አስተላልፏል። ወንድም ቭላዲሚር ዱትኪን 500,000 ሩብል (6,715 የአሜሪካ ዶላር)፣ ወንድም ቭላዲሚር ቼስኖኮቭ እና ወንድም ቫለሪ ያኮቭሌቭ ደግሞ እያንዳንዳቸው 400,000 ሩብል (5,372 የአሜሪካ ዶላር) መቀጮ እንዲከፍሉ በይኗል። ወንድሞች እስር ቤት አይገቡም።

የክሱ ሂደት

  1. ሰኔ 7, 2021

    ቭላዲሚር ቼስኖኮቭ እና ቫለሪ ያኮቭሌቭ በወንጀል ክሱ ውስጥ ተካተቱ

  2. ታኅሣሥ 30, 2020

    ቭላዲሚር ዱትኪን ክስ ተመሥርቶበት የጉዞ እገዳ ተጣለበት

  3. ኅዳር 25, 2020

    ቭላዲሚር ዱትኪን ቤቱ ከተበረበረ በኋላ የወንጀል ክስ ተከፈተበት። ለምርመራ ወደ ጣቢያ ተወሰደ

አጭር መግለጫ

ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በመንፈስ መሪነት የተጻፈውን የአምላክን ቃል ማንበባቸውና ማሰላሰላቸው በየዕለቱ የሚያጋጥሟቸውን ተፈታታኝ ሁኔታዎች ለመወጣትና ይሖዋ “በመዓት ቀን በመጠለያው” እንደሚሸሽጋቸው ለማስተዋል ረድቷቸዋል።—መዝሙር 27:5