በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በስተ ግራ፦ ወንድም ዩሪ ባራኖቭ እና ባለቤቱ ናዴዥዳ። በስተ ቀኝ፦ ወንድም ኒኮላይ ስቴፓኖቭ እና ባለቤቱ አላ

ሰኔ 8, 2022
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተለቀቀ | የእምነት አጋሮቻቸው ደግፈዋቸዋል

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተለቀቀ | የእምነት አጋሮቻቸው ደግፈዋቸዋል

ኅዳር 10, 2022 የቮልጎዳ ክልላዊ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ዩሪ ባራኖቭ እና ወንድም ኒኮላይ ስቴፓኖቭ ያቀረቡትን ይግባኝ ተመልክቶ ውሳኔ አስተላልፏል። በዩሪ ብይን ላይ ለውጥ አልተደረገም። በኒኮላይ ላይ ተላልፎ የነበረው የአራት ዓመት እስራት ግን ወደ አራት ዓመት የገደብ እስራት እንዲቀነስ ተወስኗል። ኒኮላይ ወዲያውኑ ከእስር ተለቋል።

መስከረም 5, 2022 የቮልጎዳ ከተማ ፍርድ ቤት ዩሪ እና ኒኮላይ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ዩሪ የአራት ዓመት የገደብ እስራት ተፈረደበት። በእርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም። ኒኮላይ የአራት ዓመት እስራት የተፈረደበት ሲሆን ወዲያውኑ ወህኒ ወርዷል።

የክሱ ሂደት

  1. ታኅሣሥ 19, 2019

    የደህንነት አባላት ቮልጎዳ ውስጥ የስድስት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶችን በረበሩ። ዩሪ እና ኒኮላይ ጣቢያ ተወሰዱና በዚያ እንዲቆዩ ተደረገ

  2. ታኅሣሥ 20, 2019

    ዩሪ ተፈትቶ የቁም እስረኛ ተደረገ

  3. ታኅሣሥ 23, 2019

    ኒኮላይ ማረፊያ ቤት ገባ

  4. መጋቢት 16, 2020

    ዩሪ ከቁም እስር ነፃ ተደረገ፤ ሆኖም በክስ ፋይሉ ከተካተቱ ሰዎች ጋር እንዳይገናኝ እንዲሁም ስልክና ኢንተርኔት እንዳይጠቀም ክልከላዎች ተጣሉበት

  5. ግንቦት 19, 2020

    በዩሪ ላይ የተጣሉት ክልከላዎች ተነሱለት

  6. ነሐሴ 13, 2020

    ኒኮላይ ከማረፊያ ቤት ተፈትቶ የቁም እስረኛ ተደረገ

  7. መስከረም 25, 2020

    ኒኮላይ ከቁም እስር ነፃ ተደረገ

  8. መጋቢት 7, 2022

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ወንድሞቻችን ዛሬም ለስደት አልተንበረከኩም፤ ታማኝነታቸውን ማየት በእርግጥም እምነት ያጠነክራል።—1 ተሰሎንቄ 3:7