በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ጊዬቮርግ ጊዬቮርክያን

መስከረም 21, 2022 | የታደሰው፦ ጥር 19, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “ሁሉንም ነገር አብረን እንወጣዋለን”

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “ሁሉንም ነገር አብረን እንወጣዋለን”

ጥር 17, 2023 በኒዥኒ ኖቭጎሮድ የሚገኘው የአቭታዛቮትስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ጊዬቮርግ ጊዬቮርክያን ጥፋተኛ ነው በማለት የስድስት ዓመት የገደብ እስራት በይኖበታል። እርግጥ አሁን ወህኒ አይወርድም።

የክሱ ሂደት

  1. ሐምሌ 17, 2019

    ፖሊሶች ቤቱን ፈተሹ። የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎቹንና ሰነዶቹን ወሰዱበት

  2. ሐምሌ 18, 2019

    በሥራ ቦታው በቁጥጥር ሥር ውሎ ለምርመራ ተወሰደ። ለአሥር ሰዓት ያህል እዚያው እንዲቆይ ተደረገ

  3. ነሐሴ 26, 2021

    የጉዞ እገዳ ተጣለበት

  4. ኅዳር 24, 2021

    የይሖዋ ምሥክሮችን ስብሰባ መርተሃል በሚል ክስ ተመሠረተበት

  5. ጥር 26, 2022

    ጉዳዩ ወደ አቃቤ ሕጉ ተመለሰ

አጭር መግለጫ

የጊዬቮርግ ምሳሌ እንደሚያሳየው “በመላው የወንድማማች ማኅበር ውስጥ ያሉት [ወንድሞቻችን] ተመሳሳይ መከራ እየደረሰባቸው እንዳለ” ማስታወሳችን ሁላችንም ሰይጣንን እንድንቃወምና ‘በእምነት ጸንተን እንድንቆም’ ይረዳናል።—1 ጴጥሮስ 5:9