መጋቢት 29, 2024 | የታደሰው፦ ሐምሌ 10, 2024
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “ልቤ በፍርሃት አልተሸበረም”
ሐምሌ 10, 2024 በካባሮቭስክ ግዛት የሚገኘው የካባሮቭስክ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ቫለሪ ራቦታ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል። የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶበታል። አሁን ወህኒ አይወርድም።
አጭር መግለጫ
የቫለሪን የእምነት ምሳሌ እናደንቃለን፤ ይሖዋ እሱንም ሆነ ታማኝነታቸውን የሚያስመሠክሩትን አገልጋዮቹን በሙሉ እንደሚጠብቃቸው እምነት አለን።—መዝሙር 37:28
የክሱ ሂደት
መጋቢት 1, 2022
የወንጀል ክስ ተመሠረተበት
መጋቢት 3, 2022
ቤቱ ተፈተሸ። ምርመራ ከተደረገበት በኋላ ጣቢያ እንዲያድር ተደረገ
መጋቢት 5, 2022
ወደ ማረፊያ ቤት ተላከ
ሰኔ 29, 2022
ከማረፊያ ቤት ተለቀቀ፤ የቁም እስረኛ ተደረገ
ጥቅምት 7, 2022
ከቁም እስር ተፈታ፤ የጉዞ ገደቦች ተጣሉበት
ግንቦት 11, 2023
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ