በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ቦሪስ ሲሞኔንኮ ከባለቤቱ ከኢዳ ጋር

የካቲት 1, 2023 | የታደሰው፦ ነሐሴ 1, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “መቀየር የሚያስፈልገው ያለሁበት ሁኔታ አይደለም”

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “መቀየር የሚያስፈልገው ያለሁበት ሁኔታ አይደለም”

ሐምሌ 28, 2023 በቭላድሚር ክልል የሚገኘው የኮቮርቭስኪ ከተማ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ቦሪስ ሲሞኔንኮ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን በማስተላለፍ የሁለት ዓመት ከሰባት ወር እስራት ፈርዶበታል። ሆኖም ማረፊያ ቤትና የቁም እስረኛ ሆኖ ካሳለፈው ጊዜ አንጻር የእስራት ጊዜውን እንዳጠናቀቀ ተቆጥሮለታል። ስለዚህ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።

አጭር መግለጫ

ቦሪስና ቤተሰቡ ከይሖዋ ጋር የመሠረቱት የቅርብ ወዳጅነት ለወደፊቱም ብርታትና ደስታ እንደሚሆናቸው እንተማመናለን።—1 ዜና መዋዕል 16:27

የክሱ ሂደት

  1. የካቲት 8, 2021

    ፖሊሶች የስልክ መስመሮችን ጠልፈው የቀዷቸውን ውይይቶች መሠረት በማድረግ በይፋ የወንጀል ምርመራ ጀመሩ

  2. የካቲት 17, 2021

    ቤቱ ተፈተሸ። የወንጀል ምርመራ ከተደረገበት በኋላ ጣቢያ እንዲያድር ተደረገ

  3. የካቲት 18, 2021

    የወንጀል ክስ ተመሠረተበት። በኢንተርኔት አማካኝነት የይሖዋ ምሥክሮች የሚያደርጉትን ስብሰባ መርተሃል ተብሎ ተከሰሰ። ማረፊያ ቤት ገባ

  4. ሐምሌ 13, 2021

    ከማረፊያ ቤት ተለቅቆ የቁም እስረኛ ተደረገ

  5. የካቲት 17, 2022

    ከቁም እስር ነፃ ተደረገ፤ የጉዞ ክልከላ ተጣለበት

  6. መስከረም 15, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ