ሚያዝያ 28, 2023 | የታደሰው፦ ሰኔ 16, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “ምንም ነገር ደስታዬን ሊያሳጣኝ አይችልም”
ሰኔ 15, 2023 በቭላድሚር ክልል የሚገኘው የኮቮርቭስኪ ከተማ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ሮማን አዴስቶቭ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል፤ በአንድ ዓመት እስራት እንዲቀጣም ወስኗል። ቀደም ሲል ማረፊያ ቤት ያሳለፈው ጊዜ ግምት ውስጥ ስለሚገባ አሁን ወህኒ አይወርድም።
አጭር መግለጫ
“የዘላለም ዓለት” የሆነው ይሖዋ “ሙሉ በሙሉ [በእሱ] የሚመኩትን” ምንጊዜም እንደሚጠብቃቸውና ‘ዘላቂ ሰላም እንደሚሰጣቸው’ ሙሉ እምነት አለን።—ኢሳይያስ 26:3, 4
የክሱ ሂደት
ሰኔ 28, 2021
የወንጀል ክስ ተመሠረተበት
ሐምሌ 8, 2021
ቤቱ ተፈተሸ። በቁጥጥር ሥር ዋለ
ሐምሌ 9, 2021
ማረፊያ ቤት እንዲገባ ተደረገ
ኅዳር 25, 2021
ከማረፊያ ቤት ወጥቶ የቁም እስረኛ እንዲሆን ተደረገ
ሰኔ 21, 2022
ከቁም እስር ነፃ ሆነ፤ የጉዞ እገዳ ተጣለበት
መስከረም 26, 2022
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ