በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አንድሬ ፐርሚኖቭ እና ባለቤቱ ናታሊያ

ጥቅምት 26, 2022| የታደሰው፦ ኅዳር 22, 2022
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “በአምላክ እርዳታ የማልወጣው ነገር የለም”

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “በአምላክ እርዳታ የማልወጣው ነገር የለም”

ኅዳር 21, 2022 በቼልያቢንስክ ክልል የሚገኘው የአሻ ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም አንድሬ ፐርሚኖቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ውሳኔ አስተላልፏል፤ የስድስት ዓመት የገደብ እስራትም በይኖበታል። በእርግጥ አሁን ወህኒ አይወርድም።

የክሱ ሂደት

  1. ሰኔ 11, 2021

    በአሻ እና በሚንያር ከተማ የሚኖሩ አምስት የይሖዋ ምሥክሮች ቤተሰቦች ቤት ተፈተሸ፤ የእነአንድሬ ቤት አንዱ ነው። ፖሊሶች በርካታ የግል ንብረቶቻቸውን ወረሱ

  2. ኅዳር 10, 2021

    የጉዞ እገዳ ተጣለበት

  3. ሚያዝያ 27, 2022

    የጽንፈኛ ድርጅት አባል ነህ ተብሎ ተከሰሰ፤ ከዚያም በአሸባሪዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተተ

  4. ሰኔ 6, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

እኛም እንደ አንድሬ ይሖዋ የጥንት ታማኝ አገልጋዮቹን እንዴት እንደደገፋቸው በማሰብ ብርታት ማግኘት እንችላለን። ይሖዋ “ከዚህ ቀደም እንዳደረግኩት እሸከማችኋለሁ፣ እደግፋችኋለሁ እንዲሁም እታደጋችኋለሁ” በማለት በገባው ቃል ላይ ሙሉ እምነት አለን።—ኢሳይያስ 46:4