በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ሰርጌ ኩዝኔትሶቭ

ጥር 6, 2023 | የታደሰው፦ ሚያዝያ 19, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “በይሖዋ ላይ ያለኝ እምነት ተጠናክሯል”

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “በይሖዋ ላይ ያለኝ እምነት ተጠናክሯል”

ሚያዝያ 18, 2023 በስታቭሮፖል ግዛት የሚገኘው የኔቪኖሚስኪ ከተማ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ሰርጌ ኩዝኔትሶቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል፤ የስድስት ዓመት የገደብ እስራትም ተፈርዶበታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ ሰርጌን የተንከባከበበትን መንገድ ስንመለከት በእርግጥም እሱ ‘ጭንቃችንን ሁሉ’ እንደሚያይ እንዲሁም ማንኛውም ፈተና ቢያጋጥመን ‘እንደሚያነሳንና እንደሚሸከመን’ ይበልጥ እንተማመናለን።—ኢሳይያስ 63:9

የክሱ ሂደት

  1. ኅዳር 21, 2018

    ኔቪኖሚስኪ ከተማ ውስጥ የሰርጌን ቤት ጨምሮ በበርካታ የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ላይ የብርበራ ዘመቻ ተካሄደ

  2. ታኅሣሥ 12, 2019

    የወንጀል ክስ ተመሠረተበት

  3. ሰኔ 18, 2020

    በጽንፈኝነት የተፈረጁ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተተ

  4. ግንቦት 31, 2022

    የጉዞ ክልከላዎች ተጣሉበት

  5. መስከረም 7, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ