በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ቫዲም ጊዛቱሊን

ኅዳር 25, 2022| የታደሰው፦ ታኅሣሥ 8, 2022
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “ብቻችንን እንዳልሆንን እናውቃለን”

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “ብቻችንን እንዳልሆንን እናውቃለን”

ታኅሣሥ 7, 2022 በቼልያቢንስክ ከተማ የሚገኘው የሜታለርጂቼስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ቫዲም ጊዛቱሊን ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ቫዲም የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶበታል። በእርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።

አጭር መግለጫ

እኛም ፈተናዎች ሲያጋጥሙን መቼም ብቻችንን እንዳልሆንን እርግጠኞች እንሁን። ይሖዋ ታማኝ አገልጋዮቹን ፈጽሞ አይተዋቸውም።—መዝሙር 9:9, 10

የክሱ ሂደት

  1. መጋቢት 26, 2019

    በወንድም ቭላድሚር ሱቮሮቭ ላይ ከተከፈተው የክስ መዝገብ ጋር ተያይዞ መኖሪያ ቤቱ ተፈተሸ

  2. ነሐሴ 31, 2021

    በቫዲም ላይ ክስ ተመሠረተበት። በታገደ ሃይማኖታዊ ድርጅት እንቅስቃሴ ተሳትፈሃል ተብሎ ተከሰሰ

  3. ጥቅምት 22, 2021

    መኖሪያ ቤቱ ለሁለተኛ ጊዜ ተፈተሸ። ቫዲምና ባለቤቱ ለምርመራ ተወሰዱ

  4. ሐምሌ 14, 2022

    የጉዞ እገዳ ተጣለበት

  5. ነሐሴ 18, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ