በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አሌክሳንደር ሹቶቭ

መስከረም 12, 2022 | የታደሰው፦ ሰኔ 13, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | አሌክሳንደር ሹቶቭ በይሖዋ አመራር መታመኑን ቀጥሏል

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | አሌክሳንደር ሹቶቭ በይሖዋ አመራር መታመኑን ቀጥሏል

ሰኔ 9, 2023 በካባሮቭስክ ክልል የሚገኘው የላዞ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም አሌክሳንደር ሹቶቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል፤ የሁለት ዓመት ከአምስት ወር የገደብ እስራትም ተበይኖበታል። አሁን ወህኒ አይወርድም።

የክሱ ሂደት

  1. ሐምሌ 26, 2021

    የወንጀል ክስ ተመሠረተ

  2. ሐምሌ 30, 2021

    ቤቱ ተፈተሸ። አሌክሳንደር በቁጥጥር ሥር ዋለ፣ ምርመራ ተካሄደበት፣ ከዚያም የጉዞ እገዳ ተጥሎበት ተለቀቀ

  3. ነሐሴ 3, 2021

    ስሙ በሩሲያ የጽንፈኞች ዝርዝር ውስጥ ተካተተ

  4. ሚያዝያ 28, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ስደት እየተባባሰ ሲመጣ ሁላችንም እምነታችንን ለማጠናከርና ‘ለዘላለም በአምላክ ታማኝ ፍቅር ለመታመን’ ቁርጥ ውሳኔ እናድርግ።—መዝሙር 52:8