በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ቦሪስ ያጎቪቶቭ እና ባለቤቱ ናታሊያ

መስከረም 30, 2022
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | አዎንታዊ አመለካከት መያዝ ተስፋ ላለመቁረጥ ይረዳል

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | አዎንታዊ አመለካከት መያዝ ተስፋ ላለመቁረጥ ይረዳል

ጥቅምት 10, 2022 በካባረቭስክ ክልል የሚገኘው የሶልኔችኒይ አውራጃ ፍርድ ቤት በወንድም ቦሪስ ያጎቪቶቭ ላይ ብይን አስተላልፏል። የአምስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶበታል። ቦሪስ ማረፊያ ቤት ዘጠኝ ወራት ቆይቷል። ከፍርዱ በኋላ ወዲያውኑ የተለቀቀ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ወኅኒ አይወርድም።

የክሱ ሂደት

  1. ታኅሣሥ 14, 2020

    መርማሪዎቹ፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የማወቅ ፍላጎት ያለው መስሎ የቀረበ አንድ ፖሊስና ቦሪስ ያደረጉትን ውይይት የድምፅ ቅጂ መረመሩ

  2. ግንቦት 14, 2021

    ቦሪስ የወንጀል ክስ ተመሠረተበት። የጽንፈኛ ድርጅት ስብሰባ ላይ በመገኘትና አዳዲስ አባላትን በመመልመል ወንጀል ተከሰሰ

  3. ሰኔ 5, 2021

    ቤታቸው በተፈተሸበት ወቅት እሱና ናታሊያ ምርመራ ተደረገባቸው። ከዚያም ቦሪስ ማረፊያ ቤት እንዲገባ ተደረገ

  4. ሰኔ 7, 2021

    ከማረፊያ ቤት ተለቅቆ የቁም እስረኛ ተደረገ

  5. ታኅሣሥ 29, 2021

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ። በፍርዱ ሂደት ወቅት አቃቤ ሕጉ ቦሪስ የቁም እስረኛ እያለ አንዳንድ ደንቦችን ስለጣሰ ማረፊያ ቤት እንዲገባ ጥያቄ አቀረበ። በመሆኑም ባለሥልጣናቱ ማረፊያ ቤት አስገቡት

  6. የካቲት 24, 2022

    መርማሪዎቹ አንዳንድ ደንቦችን ስለጣሱ ጉዳዩ ወደ አቃቤ ሕግ ቢሮ ተመለሰ። ያም ቢሆን ቦሪስ ከማረፊያ ቤት አልተለቀቀም

  7. ሰኔ 9, 2022

    የክሱ ሂደት ቀጠለ

አጭር መግለጫ

ቦሪስና ናታሊያ ጽድቅ በሆነውና ምስጋና በሚገባው ነገር ላይ በማተኮር ረገድ ጥሩ ምሳሌ ይሆኑናል። ‘የሰላም አምላክ’ ከእነሱ ጋር እንደሚሆን እርግጠኞች ነን።—ፊልጵስዩስ 4:8, 9

a ይህ ዜና በተዘጋጀበት ወቅት ወንድም ቦሪስ ያጎቪቶቭ ማረፊያ ቤት በመሆኑ የእሱን አስተያየት ማግኘት አልተቻለም።