ነሐሴ 25, 2023 | የታደሰው፦ ሚያዝያ 4, 2024
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “ከይሖዋ ጋር ካለኝ ወዳጅነት የበለጠ ደስታ የሚሰጠኝ ነገር የለም”
ሚያዝያ 3, 2024 በክራስኖዳር ክልል የሚገኘው የጎርያቼክልዩቼቭስኮይ ከተማ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ፓቬል ሲዶሬንኮ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል፤ የሦስት ዓመት የገደብ እስራትም በይኖበታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።
አጭር መግለጫ
እንደ ፓቬል ሁሉ እኛም “የሕይወትን መንገድ” ተከትለን ለመኖር የምናደርገው ጥረት ደስታ እንደሚያስገኝልን ስናስብ ልባችን በሐሴት ይሞላል።—መዝሙር 16:11
የክሱ ሂደት
ጥር 26, 2022
የክስ ፋይል ተከፈተበት
ጥር 28, 2022
ቤቱ ተፈተሸ እንዲሁም ምርመራ ከተደረገበት በኋላ የጉዞ ገደብ ተጣለበት
መጋቢት 22, 2023
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ