የካቲት 16, 2022 | የታደሰው፦ ግንቦት 10, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | ወንድም ኢቫን ሹልዩክ በትዕግሥት ስደትን ተቋቁሟል
ግንቦት 10, 2023 በክራስናያርስክ ክልል የሚገኘው የናዛሮቭስኪ ከተማ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ኢቫን ሹልዩክ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል፤ የሰባት ዓመት የገደብ እስራትም ፈርዶበታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።
የክሱ ሂደት
ሰኔ 18, 2020
የታጠቁ ፖሊሶች የእነ ኢቫን ሹልዩክን ቤት ከበረበሩ በኋላ ኢቫንን በቁጥጥር ሥር አዋሉት። ከዚያም ጊዜያዊ ማረፊያ ቤት ውስጥ አቆዩት
ሰኔ 19, 2020
ፍርድ ቤቱ ኢቫን ወደ ማረፊያ ቤት እንዲዛወር አዘዘ
ሐምሌ 9, 2020
ከማረፊያ ቤት ተለቀቀ። ከቤቱ ውጪ ያለፈቃድ ማንንም እንዳያነጋግር ተከለከለ። ከጠዋቱ 12:00 እስከ ምሽቱ 5:00 ባለው ጊዜ ከቤት እንዳይወጣ ታገደ፤ በመሆኑም ሥራ መሥራት አልቻለም
ነሐሴ 14, 2020
መርማሪው በኢቫን ላይ የተጣሉት እገዳዎች እንዲራዘሙ ፈልጎ ነበር፤ ሆኖም ኢቫን ጥሩ ስም ስለነበረው ጥያቄው ተቀባይነት አላገኘም። አብዛኞቹ እገዳዎች ተነሱለት
ነሐሴ 17, 2020
የጉዞ እገዳ ተጣለበት
መስከረም 15, 2021
የፍርድ ሂደቱ ጀመረ
አጭር መግለጫ
“ይሖዋ፣ ለአምላክ ያደሩ ሰዎችን ከፈተና እንዴት እንደሚያድን . . . ያውቃል”፤ ይህን በማወቃችን ምንኛ አመስጋኞች ነን!—2 ጴጥሮስ 2:9