በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ዲሚትሪ ዶልዢኮቭ እና ባለቤቱ ማሪና

ግንቦት 2, 2023 | የታደሰው፦ ሐምሌ 3, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | የእምነት ምሳሌዎች አበረታተውታል

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | የእምነት ምሳሌዎች አበረታተውታል

ሰኔ 30, 2023 በኖቮሲቢርስክ የሚገኘው የሌኒንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ዲሚትሪ ዶልዢኮቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን በማስተላለፍ የሦስት ዓመት እስራት ፈርዶበታል። ዳኛው፣ ፍርዱ እስራት መሆኑ ቀርቶ በጉልበት ሥራ ካምፕ ሦስት ዓመት እንዲሠራ በይኗል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም። በጉልበት ሥራ ካምፕ በሚሠራበት ወቅት ከደሞዙ 10 በመቶው ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል። ከከተማው መውጣትም አይችልም።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ፣ የዲሚትሪንም ሆነ የሁሉንም አገልጋዮቹን እምነትና ጽናት እንደሚያስተውል ብሎም እንደሚያበረታታቸው እርግጠኞች ነን።—ራእይ 2:19

የክሱ ሂደት

  1. ግንቦት 13, 2022

    የክስ ፋይል ተከፈተበት

  2. መስከረም 8, 2022

    መኖሪያ ቤቱ ተፈተሸ። ጣቢያ እንዲያድር ተደረገ

  3. መስከረም 9, 2022

    ምርመራ ተደረገበት፤ ከዚያም ከቼልያቢንስክ 1,500 ኪሎ ሜትር በላይ ርቆ በኖቮሲቢርስክ ወደሚገኝ ማረፊያ ቤት በአውሮፕላን ተወሰደ

  4. ኅዳር 11, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  5. ኅዳር 24, 2022

    ከማረፊያ ቤት ተለቅቆ የቁም እስረኛ ተደረገ