የካቲት 16, 2023 | የታደሰው፦ መስከረም 21, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “ይሖዋ ላደረገልን መንፈሳዊ ዝግጅቶች ያለኝ አድናቆት ጨምሯል”
መስከረም 15, 2023 በቭላድሚር ክልል የሚገኘው የኮቭሮቭስኪ ከተማ ፍርድ ቤት፣ ወንድም አሌክሲ ኩፕሪያኖቭ ጥፋተኛ ነው በማለት የአንድ ዓመት እስራት ፈረደበት። ሆኖም በማረፊያ ቤትና በቁም እስር ካሳለፈው ጊዜ አንጻር የእስር ጊዜውን እንደጨረሰ ተቆጥሮለታል። አሁን ወህኒ አይወርድም።
አጭር መግለጫ
እኛም ከይሖዋ ዝግጅቶች ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ቆርጠናል፤ “የዲያብሎስን መሠሪ ዘዴዎች መቋቋም” የሚያስችለንን “ሙሉ የጦር ትጥቅ” መልበስ የምንችለው እንዲህ ካደረግን ነው።—ኤፌሶን 6:11
የክሱ ሂደት
የካቲት 17, 2021
ባለሥልጣናት ሰባት የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች ፈተሹ፤ አንደኛው የወንድም አሌክሲ ቤት ነበር። ሃያ ሦስት ወንድሞችና እህቶች ምርመራ ተደረገባቸው
ሰኔ 28, 2021
የወንጀል ክስ ተመሠረተበት። ስብሰባዎች ላይ በመገኘቱ ‘በጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴ ተሳትፈሃል’ በሚል ተከሰሰ
ሐምሌ 8, 2021
ቤቱ ለሁለተኛ ጊዜ ተፈተሸ። ምርመራ የተደረገበት ሲሆን ጣቢያ እንዲያድር ተደረገ
ሐምሌ 9, 2021
ወደ ማረፊያ ቤት ተላከ
ኅዳር 19, 2021
ከማረፊያ ቤት ተለቀቀ፤ ከዚያም የቁም እስረኛ ተደረገ
ሰኔ 21, 2022
በቁም እስር ምትክ ሌሎች የጉዞና የእንቅስቃሴ ክልከላዎች ተጣሉበት
ጥቅምት 4, 2022
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ