በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ዩሪ ችዬርኒክ

ሚያዝያ 26, 2023 | የታደሰው፦ ጥቅምት 3, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | ‘ይሖዋ በሁለት እጆቹ ይዞናል’

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | ‘ይሖዋ በሁለት እጆቹ ይዞናል’

መስከረም 28, 2023 የፕሮኮፕዬቭስክ አውራጃ ማዕከላዊ ፍርድ ቤት ወንድም ዩሪ ችዬርኒክ ጥፋተኛ ነው በማለት ለሦስት ዓመት የጉልበት ሥራ እንዲሠራ ፈርዶበታል። a አሁን ወህኒ አይወርድም።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ ታማኝ አገልጋዮቹ በታማኝነት ለመጽናት ጥረት ሲያደርጉ ምንጊዜም ‘ሰላማቸውን እንደ ወንዝ’ እንደሚያበዛላቸው ሙሉ እምነት አለን።—ኢሳይያስ 48:18

የክሱ ሂደት

  1. ሐምሌ 12, 2020

    ቤታቸው ተፈተሸ። ዩሪ እና የሌና ምርመራ ተካሄደባቸው

  2. ኅዳር 5, 2021

    የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው

  3. ኅዳር 10, 2021

    ለሁለተኛ ጊዜ ቤታቸው ተፈተሸ

  4. ሚያዝያ 26, 2022

    ዩሪ የጉዞ እገዳ ተጣለበት

  5. ሐምሌ 18, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

a የጉልበት ሥራ እንዲሠራ የተፈረደበት ሰው፣ ባለሥልጣናቱ የሚሰጡትን ሥራ ማከናወን ያለበት ሲሆን ከ5 እስከ 20 በመቶ የሚሆነው የደሞዙ ክፍል ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል። ባለሥልጣናቱ ፍርደኛው ተባባሪ እንዳልሆነ ወይም ለመሥራት ፈቃደኛ እንዳልሆነ ከወሰኑ ሰውየው ወህኒ ይወርዳል።