መጋቢት 22, 2023 | የታደሰው፦ ሚያዝያ 28, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “ይሖዋ የሚጠብቅብኝን ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ቆርጫለሁ”
ሚያዝያ 28, 2023 በቼልያቢንስክ ክልል የሚገኘው የአሻ ከተማ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ቫዲም ፍዮዶሮቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል፤ የስድስት ዓመት የገደብ እስራትም ፈርዶበታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።
አጭር መግለጫ
እንደ ቫዲም ሁሉ እኛም፣ ይሖዋ እሱን ተስፋ የሚያደርጉትንና ‘መንገዱን የሚከተሉትን’ እንደሚባርካቸውና እንደሚያበረታቸው እንተማመናለን።—መዝሙር 37:34
የክሱ ሂደት
ሰኔ 11, 2021
የደህንነት ኃይሎች የቫዲምን እና የልጁን የአንድሬን ቤት በረበሩ
ሚያዝያ 29, 2022
ቫዲም የወንጀል ክስ ተመሠረተበት
ታኅሣሥ 1, 2022
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ