በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ቫለሪ ቭያዝኒኮቭ

ሐምሌ 11, 2023 | የታደሰው፦ ኅዳር 9, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | ‘ይሖዋ ፈጽሞ አይተወኝም’

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | ‘ይሖዋ ፈጽሞ አይተወኝም’

ኅዳር 7, 2023 በፕሪሞርይስ ግዛት የሚገኘው የፖዣርስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ቫለሪ ቭያዝኒኮቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ውሳኔ አስተላልፏል። ወንድም ቫለሪ የሁለት ዓመት ከስድስት ወር የገደብ እስራት ተበይኖበታል። አሁን ወህኒ አይወርድም።

አጭር መግለጫ

እኛም ልክ እንደ ቫለሪ የአምላክ ቃል ባለው ኃይል ላይ ምንጊዜም ከተማመንን የሚያጋጥሙንን መከራዎች ሁሉ በጽናት እንደምንቋቋም መተማመን እንችላለን።—ዕብራውያን 4:12

የክሱ ሂደት

  1. 2018

    መርማሪዎች በሉቺጎርስክ ከተማ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮችን በድብቅ መከታተል ጀመሩ። አንድ ሰላይ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ማወቅ የሚፈልግ መስሎ በአካባቢው ያሉ የይሖዋ ምሥክሮችን በመቅረብ ከእነሱ ጋር ያደረገውን ውይይት በድብቅ ቀዳ

  2. ሐምሌ 16, 2021

    ቫለሪ የክስ ፋይል ተከፈተበት። ክሱ ‘እገዳ በተጣለበት ድርጅት እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ ሌሎችን አነሳስቷል’ የሚል ነበር

  3. ታኅሣሥ 5, 2022

    የጉዛ እገዳዎች ተጣሉበት

  4. የካቲት 9, 2023

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ