የካቲት 3, 2022 | የታደሰው፦ ሐምሌ 20, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈታ | ወንድም አሌክሲ ኡክሆቭ መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ማንበቡና ማሰላሰሉ በይሖዋ እንዲታመን ረድቶታል
ሐምሌ 18, 2023 የካባረቭስክ ክልል ፍርድ ቤት፣ በወንድም አሌክሲ ኡክሆቭ ላይ የተፈረደበት የስድስት ዓመት ተኩል እስራት ወደ ስድስት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት እንዲለወጥ ወሰነ። አሌክሲ ውሳኔው ከተላለፈ ብዙም ሳይቆይ ከእስር ተፈትቷል።
መጋቢት 24, 2023 በካባረቭስክ ክልል የሚገኘው የሶቪየትስኮ ጋቫንስኪ ከተማ ፍርድ ቤት አሌክሲ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል። የስድስት ዓመት ተኩል እስራት ተበይኖበታል። ወዲያውኑ ወደ እስር ቤት ተወስዷል።
የክሱ ሂደት
ጥቅምት 22, 2020
የፌዴራል ደህንነት አባላት የወንድም ኡክሆቭን ቤት ፈተሹ። የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎችን፣ ፍላሽ ድራይቮችን፣ ሲም ካርዶችን፣ የባንክ ካርዶችን፣ የግል ሰነዶችን እንዲሁም የታተሙ ጽሑፎችን ወረሱ። መርማሪዎች አሌክሲን ማረፊያ ቤት አስገቡት
ጥቅምት 23, 2020
ፍርድ ቤቱ አሌክሲ ማረፊያ ቤት እንዲቆይ አዘዘ
ሐምሌ 9, 2021
ከማረፊያ ቤት ተለቀቀ፤ ሆኖም ታስሮበት ከነበረው ከኮምሶሞልስክ ኦን አሙር አካባቢ እንዳይወጣ ታዘዘ
መስከረም 6, 2021
ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
አሌክሲ ‘በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን በአደራ በመስጠቱ’ ይሖዋ ወሮታ እንደሚከፍለው እርግጠኞች ነን።—1 ጴጥሮስ 2:23